ሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ ትርኢት ልታሳይ ነው፡፡

ባህርዳር፡ጥር የካቲት 1 /2010 ዓ/ም(አብመድ)የሰሜን ኮሪያ ዓመታዊ የወታደራዊ ትርኢት በሚያዝያ ወር የሚካሄድ ቢሆንም በነገው ዕለት ከሚከፈተው የበጋ ኦሊምፒክ ቀድማ በዛሬው ዕለት ልታካሂድ መሆኗን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ደቡብ ኮሪያ የበጋ ኦሎምፒክ በምታስጀምርበት ዋዜማ የሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ ትርኢት ሊቀርብ መሆኑ በአካባቢው ስጋት እንደሚፈጥር ተነግሯል፡፡

የሰሜን ኮሪያ ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያም ወታደራዊ ትርኢቱ ከመካሄዱ ቀደም ብሎ የሀገር ፍቅርን የሚቀሰቅሱ ፕሮግራሞችን ማሳየት ጀምሯል፡፡

የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት እንደገለጹትም ባለፈው ወር ላይ 13 ሺህ ወታደሮች በፕዮንግያንግ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ልምምድ ሲያደርጉ ተስተውለዋል ብለዋል፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3693131
  • Unique Visitors: 209286
  • Published Nodes: 2809
  • Since: 03/23/2016 - 08:03