የኢራን ፕሬዝዳንት ያለሶሪያ ፈቃድ ጣልቃ የሚገቡ ሀገራትን አስጠነቀቁ፡፡

ባህርዳር፡ጥር 30/2010 ዓ/ም(አብመድ)የራሳቸውን ብሄራዊ ጥቅም ፍለጋ የሶሪያን ሉአላዊነት የሚጥሱ ሀገራት ከጣልቃ ገብነታቸው እንዲታቀቡ የኢራን ፕሬዝዳንት ማስጠንቀቃቸውን ፕሬስ ቲቪ ዘገበ ፡፡

የኢራን ፕሬዝዳንት ሀሰን ሩሃኒ ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ ባደረጉት ቆይታ ሶሪያ በህገወጥ ወራሪዎች እየፈረሰች ነው ብለዋል፡፡

የአሜሪካ ጣልቃ ገብነት ተቀባይነት የሌለው ነው ያሉት ሃሰን ሩሃኒ ቴህራን እና ሞስኮ በሶሪያ ጉዳይ በጋራ እንደሚሰሩ አረጋግጠው ውሳኔው የሶሪያ ህዝቦች እንጂ የሌሎች ሀገራት ሊሆን አይገባም ብለዋል፡፡

የሶሪያ መንግስት እና ህዝብ ድምፅ ሊከበር እንደሚገባም በመናገር ሁለቱ ሃገራት የሶሪያን ሰላም ለመመለስ ከቱርክ ጋር በጋራ ለመስራት ያቀዱ ሲሆን የጋራ ጉባኤ ለመጥራትም ተስማምተዋል፡፡

ሶሪያ በውስጥ ተቃዋሚዎች እና በውጭ ጣልቃ ገቦች ሰላሟን ተንጥቃ መፈራረስ ከጀመረች ሰባት አመታት ማስቆጠሯን ዘገባው አስታውሷል ፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3870360
  • Unique Visitors: 214840
  • Published Nodes: 2859
  • Since: 03/23/2016 - 08:03