የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ማሪታይም ተቋም የባህር ላይ ምህንድስና ተማሪዎችን አስመረቀ፡፡

ባህርዳር፡ጥር 30/2010 ዓ/ም(አብመድ)ዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በሜካኒካል እና ኤሌክትሪካል ምህንድስና ያገኙ 62 ተማሪዎችን ተቀብሎ በባህር ላይ ምህንድስና በማሠልጠን አስመርቋቸዋል፡፡

Image may contain: 1 person, standing

በምረቃ ስነስርአቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የባህር ምህንድስና ተቋም ዋና አሰልጣኝ ካፒቴን ሲደሪቱ አጉንተሪ ለተመራቂዎች ባደረጉት ንግግር ‹‹ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እውቀት ስለቀሰማችሁ በዘርፉ ብቁ ተወዳዳሪዎች ናችሁ፡፡

 

ከዚህ በኋላ በዓለም አቀፉ ገበያ ገብታችሁ ሀገራችሁን ማገልገል ይጠበቅባችኋል ››ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ 
የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፍሬው ተገኝ በበኩላቸው የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የባህር ላይ የምህንድስና ዘርፉን ለማሳደግ ይሰራል በማለት ለተመራቂዎች ባስተላለፉት የስራ መልዕክት ‹‹እናንተ የሀገራችሁ አምሳደሮች ናችሁ፡፡ በስልጠና ቆይታችሁም አርአያዎች ስለነበራችሁ የእናንተን የመማር ማስተማር ስነ ዘዴ ወደ ሌሎች የትምህርት ዘርፎች ለማስፋት እንሰራለን›› ብለዋል፡፡
Image may contain: one or more people, people standing and outdoor

 

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በየአመቱ በተለያዩ ዙሮች ከ 500 በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ሲሆን ይሄን አሃዝ ከፍ ለማድረግ በእቅድ እየተሰራ ነው፡፡ 
አባይ እና ጣናን ተንተርሶ የተመሰረተው የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ማሪታይም ተቋም የባህር ምህንድስና ትምህርት በማስተማር ከሃገራችን የመጀመሪያው ነው፡፡

በአፍሪካ ደረጃ 10 የሚደርሱ ሀገራት ብቻ የባህር ምህንድስናን የሚያስተምሩ ሲሆን ከነዚህም መካከል ኢትዮጵያ፣ግብፅ፣ ደቡብ አፍሪካ፤ጋና እና ናይጄሪያ በአብነት ይጠቀሳሉ፡፡ Image may contain: one or more people, people standing and outdoor
የባህር ዳር ዩኒቨርስቲም በኤሌክትሪካል እና ኬሚካል ምህንድስና ትምህርት ዘርፎች የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙ ተመራቂዎችን አወዳድሮ ያስመርቃል፡፡

ወደባህር ምህንድስና ተቋም ለመግባት የሚያመለክቱ ተወዳዳሪዎች ከትምህርት ማስረጃቸው በተጨማሪ ጤንነታቸው በህክምና የተረጋገጠ መሆን ይገባዋል ፡፡ዕድሜያቸውም ከ26 አመት በታች የሆኑ ወንዶችን ብቻ ነው ተቀብሎ የሚያስተምረው ፡፡ 
ከዚህ ተቋም የሚወጡ ተመራቂዎች በአለም አቀፍ የመርከብ ድርጅቶች ተቀጥረው የመስራት ዕድላቸው ሠፊ እንደሆነ ሲገለጽ ለሀገራቸው የሙያ ወኪል ሆነውም ያገለግላሉ፡፡

አስተያየት የሠጡን አንዳንድ ተመራቂዎች እንደተናገሩት ስልጠናው አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እና ትምህርቱ በተግባር የተደገፈ በመሆኑ ስራ ላይ ችግር አይፈጥርብንም ብለዋል ፡፡
የሺሀሳብ አበራ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3884811
  • Unique Visitors: 215544
  • Published Nodes: 2870
  • Since: 03/23/2016 - 08:03