ሁሉም የደቡብ አፍሪካ ማዕድን ሠራተኞች ያለምንም ጉዳት ከጉድጓዱ ወጡ

ባህርዳር፡ጥር 25/2010 ዓ/ም(አብመድ)በኤሌክትሪክ መቋረጥ ምክኒያት ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ በወርቅ ማዕድን ማውጫ ጉድጓድ ውስጥ ቀርተው የነበሩት 955 የማዕድን ሠራተኞች ያለምንም ጉዳት መውጣታቸውን ቢቢሲ ዘገበ ፡፡

ከጆሃንስበርግ ደቡብ ምዕራብ 290 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው ዌልኮም ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው ቤትሪክስ የማዕድን ማውጫ ሲባንዬ ስቲልዋር በተባለ ኩባንያ የሚተዳደር ሲሆን 1 ሺ ሜትር ጥልቀት እና 23 ደረጃዎች ያሉት ነው ፡፡

ለኤሌክትሪክ መቋረጡ በምክኒያትነት የቀረበው ከማዕድኑ አቅራቢያ በሚገኝ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ተሸካሚ መስመር ላይ ነጎድጓድ የቀላቀለ ዝናብ በመከሰቱ ሳይሆን አይቀርም ተብሏል ፡፡

ሆኖም የኤሌክትሪክ መስመሩ በመስተካከሉ ምክኒያት የተቋረጠው ሃይል ተስተካክሎ የማዕድን ማውጫው የአየር ማቀዝቀዣ እና ሊፍቱ በመስራቱ ሠራተኞቹን በሰላም ወደምድር ማውጣት ተችሏል ፡፡

የሲባንዬ ስቲልዋተር የማዕድን ኩባንያ ቃል አቀባይ የሆነው ጀምስ ዌልስቴድ ሠራተኞቹ ለሁለት ቀናት በማዕድን ጉድጓዱ ውስጥ ቆይተው በወጡበት ወቅት እንደተናገረው ‹‹ከአንዳንድ የድርቀት እና የደም ግፊት መጨመር በስተቀር የታየባቸው የጎላ ችግር የለም ››ብለዋል፡፡

እ.ኤ.አ ከ2017 ጀምሮ በደቡብ አፍሪካ ከ80 የበለጡ የማዕድን ማውጫ ስፈራዎች ላይ አደጋ መድረሱን ቢቢሲ ዘግቧል ፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3693130
  • Unique Visitors: 209286
  • Published Nodes: 2809
  • Since: 03/23/2016 - 08:03