የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሊቢያ ለሚካሄደው ምርጫ ድጋፍ እንደሚሰጥ አስታወቀ፡፡

ባህርዳር፡ጥር 04 /2010 ዓ/ም(አብመድ)የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በ 2018 መጨረሻ ላይ በሊቢያ ለሚከናወነው ምርጫ ድጋፍ እንደሚሰጥ ማስታወቁን ሮይተርስ ዘገበ ፡፡
ምርጫው ሊቢያን ለማረጋጋት እንደሚረዳ ድርጅቱ ጠቅሶ ለአስተባባሪው አካል ድጋፍ ከመስጠት በተጨማሪ ዜጎች መሪያቸውን ለመምረጥ እንዲመዘገቡ የተለያዩ ድጋፎች እንደሚያደርግ አስታውቋል ፡፡


ሊቢያን ለረጅም ጊዜ የመሩት ሙአማር ጋዳፊ እ.ኤ.አ በ2011 በሕዝባዊ አመጽ ከተወገዱ በኋላ ሃገሪቱ ወደ እርስ በእርስ ግጭት ገብታ በመቆየቷ ያሁኑ ምርጫ ሰላምና መረጋጋት ሊያመጣ ይችላል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል፡፡


የተለያየ አመለካከት ይዘው በተነሱ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ሃይሎች በተከፋፈለች ሀገር ውስጥ ምርጫን ማካሄድ አስቸጋሪ ነው የሚለው ድርጅቱ በ2014 በተካሄደው ምርጫ የመንግስት ተቃዋሚዎች ለግጭቱ ዋና ምክንያት ነበሩ ሲል ይወቅሳል፡፡


በአሁኑ ሰዓት በአብዛኞቹ የሊቢያ ግዛቶች የጸጥታ እና ደህንነት ጉዳይ አስቸጋሪ መሆኑን የገለጸው ሮይተርስ አዲስ የምርጫ ህግ ማውጣትና ህገ መንግስት የማሻሻል ስራ ከአገር አቀፍ ምርጫ በፊት ሊከናወን ይገባል የሚሉ ወገኖች መኖራቸውን ጨምሮ ዘገቧል ፡፡ 
የሊቢያ ሕዝብ ሁሉን አሳታፊ እና ተቀባይነት ያለው ምርጫ እንዲካሄድ ድጋፉን በመስጠት ላይ ሲሆን እስካሁን በድምሩ 1ሚሊየን 965 ሺ 450 ህዝብ ድምጽ ለመስጠት መመዝገቡን የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል ፡፡ 
እ.ኤ.አ.በ2014 በሊቢያ በተካሄደው ምርጫ 630 ሺ ህዝብ ብቻ ተሳትፎ ማድረጉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3537522
  • Unique Visitors: 199678
  • Published Nodes: 2652
  • Since: 03/23/2016 - 08:03