የተባበሩት መንግስታት እስራኤል ለአፍሪካውያን ስደተኞች ሌሎች መፍትሄዎችን እንድታፈላልግ ጥሪ አቀረበ፡፡

ባህርዳር፡ጥር 03 /2010 ዓ/ም(አብመድ)የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ እስራኤል በሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን  ስደተኞችን ወደሃገራቸው ከመመለስ ይልቅ የተለየ መፍትሄ እንድትፈልግ ጥሪ ማቅረቡን ሮይተርስ ዘገበ ፡፡Image result for un

አንዳንዶች በአውሮፓ ወይም ሌሎች አገራት ውስጥ ሊሰፈሩ ይችላሉ ብሏል ድርጅቱ በላከው መግለጫ፡፡

እስራኤል የኤርትራ እና የሱዳን ስደተኞችን ከሰሃራ በታች ወዳሉ የአፍሪካ ሃገራት ለመላክ ያወጣችውን ፖሊሲ ማቆም አለባት ሲሉ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ዊሊያም ስፓይንድለር በጄኔቫ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ወደሀገሬ ገብተዋል በሚል እስራኤል በሺዎች የሚቆጠሩ የአፍሪካ ስደተኞች ከሃገሯ እንዲወጡ የጊዜ ገደብ አስቀምጣ በቅርቡ ያስተላለፈችውን ውሳኔ ተከትሎ ነው የኮሚሽነሩ መግለጫ የወጣው ፡፡ 

የፖለቲካም ሆነ የኢኮኖሚ ጥገኘነት ፈልገው እስራኤል የገቡ አፍሪካውያን ስደተኞች 3ሺ 500 የአሜሪካ ዶላር እየተቀበሉ በ3 ወራት ውስጥ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ለመመለስ ወይም ወደ "ሶስተኛ ሀገር" እንዲሄዱ ለማድረግ ነው እስራኤል በቅርቡ መግለጫውን ያወጣቸው ፡፡

በአሁኑ ወቅት 27 ሺ ኤርትራውያን እና 7ሺ 700 ሱዳናውያን በእስራኤል ሲኖሩ ሩዋንዳ እና ኡጋንዳ  ስደተኞችን የመቀበል ፍላጎት እንደሌላቸው ተዘግቧል ፡፡

 

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3158921
  • Unique Visitors: 186665
  • Published Nodes: 2579
  • Since: 03/23/2016 - 08:03