ሃገራችን ሰላሟ ተመልሶ በሰላም ትምህርታችንን መከታተል እንፈልጋለን ፡-የደቡብ ሱዳን ህጻናት

ባህር ዳር፡ ሰኔ 12 /2009 ዓ/ም (አብመድ)ደቡብ ሱዳን ውስጥ የተከሰተው አለመረጋጋት ማህበረሰቡ ቀየውን ለቆ ለእንግልት እየተዳረገ ሲሆን የዚህ ገፈት ቀማሽ በመሆን የፊት መስመሩን የሚይዙት ህጻናት ናቸው ፡፡አሁን ላይ በደቡብ ሱዳን በተፈጠረው አለመረጋጋት ከ100ሺህ በላይ ሰዎች ለስደት የተዳረጉ ሲሆን አብዛኞዎቹ ህጻናት ናቸው፡፡

በደቡብ ሱዳን አሁን ላይ ከ10ሺህ በላይ ህጻናት አስፈላጊው እንክብካቤ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን አካባቢያቸው ሰላም ውሎ ሰላም እንዲያድር ተስፋ ያደረጉ ሲሆን ሰላምን በማስፈን በኩል የሚመለከታቸው አከላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ተማጽነዋል፡፡

የወደፊቷ ደቡብ ሱዳን እጣፈንታ የሚወሰነው አሁን ባሉት ህጻናት ነው የሚሉት የደቡብ ሱዳን ህጻናት ትምህርት ለመማር የሚያስችል ሁኔታ በአካባቢያቸው እንዲፈጠር ጠይቀዋል፡፡

ምንጭ፡-አናዶሉ 

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3161802
  • Unique Visitors: 186711
  • Published Nodes: 2579
  • Since: 03/23/2016 - 08:03