Latest News

ባህር ዳር፡ መስከረም 17 /2010 ዓ/ም (አብመድ)የሶማሊያ አየር ኃይል መኮንን የነበሩት የአህጉሩ የመጀመሪያዋ ሴት አውሮፕላን አብራሪ ፓይለት ከሁለት አስርት አመታት የውጭ ስደት ቆይታ በኋላ በሃገራቸው ግልጋሎት ለመስጠት ወደ ሶማሊያ መግባታቸውን መንግስት አስታውቋል፡፡

ባህር ዳር፡ መስከረም 17 /2010 ዓ/ም (አብመድ)የቻድ መንግሥት በአዲሱ የጉዞ ማዕቀብ ላይ አገሪቷን የአሜሪካ ባለስልጣናት ለምን ማካተት እንደፈለጉ ግልጽ አይደለም ብለዋል፡፡
ባለፈው እሁድ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከቻድ በተጨማሪ ሌሎች ከሰባት ሀገሮች የሚመጡ ዜጎች ላይ አዳዲስ የጉዞ ክልከላዎች መደረጉ ይታወሳል፡፡

ባህር ዳር፡ መስከረም 17 /2010 ዓ/ም (አብመድ)የታንዛኒያ መንግስት በኢንተርኔት የሚጻፉ ጹሁፎችን በተመለከተ ረቂቅ የፖሊሲ ህግ ማዘጋጀቱን አስታውቆ፤ የኦላይን መገናኛ ብዙሃን ህገ-ወጥነትን ለመከላከል እና በሃገሪቱ ውስጥ ባሉ የተለያዩ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ቡድኖች ውስጥ ህግን የተከተለ አሰራር እንዲኖር ለማድረግ ያለመ ረቂቅ ህግ መሆኑን ይገልጻል፡፡

ባህር ዳር፡ መስከረም 17 /2010 ዓ/ም (አብመድ)በኢትዮጵያ ባሉት የኢንቨስትመንት እድሎችና አማራጮች የጣልያን ባለሃብቶች ቢሰማሩ ውጤታማ እንደሚሆኑ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ገለጹ።

ባህር ዳር፡ መስከረም 17 /2010 ዓ/ም (አብመድ)የመስቀል ደመራ በዓል ከሃይማኖታዊነቱም ባለፈ የሠላምና የአብሮነት ዓርማ በመሆኑ ይህንኑ ዕሴቱን ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ   አቡነ ማትያስ ገለጹ።... More

ባህር ዳር፡ መስከረም 17 /2010 ዓ/ም (አብመድ)ትናንት ምሽት በድምቀት በተከበረው የደመራ በዓል ላይ ብጹዕ አቡነ አብርሀም የባህር ዳርና ምዕራብ ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እንዳሉት መስቀል የፍቅር የመተሳሰብ፣አንድነት እና ከራስ ወዳድነት ተላቆ ለእኔ ማለት ቀርቶ ለእኛ ማለት ነው፡፡

ባህር ዳር፡ መስከረም 16 /2010 ዓ/ም (አብመድ)በአማራ ክልል  ዋነኛ  የቱሪዝም  መዳረሻ በሆኑት  ጎንደር እና ባህር ዳር  ከተሞች  ያለው የጸጥታ  ሁኔታ  ለጎብኝዎች ምቹ  መሆኑን  በጎንደርና ባህር ዳር  ቆይታ ያደረጉት  የብሪታንያ ኢምባሲ የፖለቲካ ጉዳዮች  ዘርፍ ሀላፊ ኦሊስተር  አርኖልድ  ተናገሩ፡፡

 

ባህር ዳር፡ መስከረም 16 /2010 ዓ/ም (አብመድ)የብሪታንያ ኢምባሲ የፖለቲካ ጉዳዮች ዘርፍ ሀላፊ ኦሊስቴር አርኖልድ በአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ከእንግሊዝኛ አገልግሎት ጋር ባደረጉት  ቆይታ እንደገለጹት ሀገራቸው ለበርካታ ዓመታት  የኢትዮጵያ  ልማት ዘርፍ ዋነኛ አጋር ሆና ስትሰራ መቆየቷን አስታውሰው፣በተለይም በትምህርቱ ዘርፍ በሚደረገው ልማት በስፋት እየሰራች መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

 

 

ባህር ዳር፡ መስከረም 15 /2010 ዓ/ም (አብመድ)የኦሮሚያ ክልላዊ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 57 ንዑስ አንቀፅ ሶስት ፕሬዝዳንቱ በወንጀል ድርጊት ጥፋተኛ ተብለው ለተፈረደባቸው የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረግ እንደሚችሉ ይደነግጋል።

 

በዚህም መሠረት የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ በክልሉ ባሉ 36 ማረሚያ ቤቶች በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብለው የእስር ጊዜያቸውን በማሳለፍ ላይ ለነበሩ 6 ሺህ 655 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጋቸውን በክልሉ ፍትህ ቢሮ የኮሙኒኬሽን ስራ ሂደት መሪ አቶ መለሰ ዓባይነህ ተናግረዋል።

 

ባህር ዳር፡ መስከረም 15 /2010 ዓ/ም (አብመድ)ኢትዮጵያ 90 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የሚጠይቅ የ15 አመት ብሔራዊ የአየር ንብረት ለውጥ መቆጣጠሪያ እቅዷን ይፋ አደረገች።

 

እቅዱ በአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር አስተባባሪነት የተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ የክልል የአየር ንብረት ለውጥ መቆጣጠሪ ቢሮ ሃላፊዎች እንዲሁም የአለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት ዛሬ በአዲስ አበባ ይፋ ተደርጎ ውይይትም ተካሂዶበታል።

 

Pages

Video News

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች ፈጣንና ሁሉን አውዳሚ ተምች በመከላከል አርአያነታቸውን አሳይተዋል
በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች ፈጣንና ሁሉን አውዳሚ ተምች በመከላከል አርአያነታቸውን አሳይተዋል
ጐንጅ ቆለላ እና በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጃዊ ወረዳዎች ፈጣንና ሁሉን አውዳሚ ተምችን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ጐንጅ ቆለላ እና በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጃዊ ወረዳዎች ፈጣንና ሁሉን አውዳሚ ተምችን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

Amharan News

Ethiopian News

Visitors

  • Total Visitors: 2319387
  • Unique Visitors: 136353
  • Published Nodes: 2118
  • Since: 03/23/2016 - 08:03