Latest News

የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ኢትዮጵያ ባቀረበችው ጥያቄ መሰረት የምህረት አዋጁን በድጋሚ ለአንድ ወር አራዝሟል።

ባህር ዳር፡ ሐምሌ 19 /2009 ዓ/ም (አብመድ) በየቀኑ የሚዋጠውን የጸረ -ኤች አይ ቪ ኤድስ መድሃኒት በመርፌ በሚሰጡ መድሃኒቶች ለመተካት እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን የ ምርምሩን እያከናወኑ ያሉ የሳይንስ ሊቃውንት መናገራቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገበ ፡፡

 

ባህር ዳር፡ ሐምሌ 18 /2009 ዓ/ም (አብመድ)መንግስት በሙስና የተጠረጠሩ ከ30 በላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ ደላሎች እና ነጋዴዎችን ዛሬ በቁጥጥር ስር አውሏል።
የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ፥ መንግስት ከሙስና ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር በዋሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ግለሰቦች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸው 31 ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ ደላሎች እና ነጋዴዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ተናግረዋል።

ባህር ዳር፡ ሐምሌ 18 /2009 ዓ/ም (አብመድ)አብዛኛው ህንዳዊ ከሚያገለው ዳሊት ማህበረሰብ የተገኙት የቀድሞው ጠበቃ እና ሀገረ ገዢ ራም ናዝ ኮቪንድ ሰሞኑን ከህንድ ፓርላማና ከክልል ምክር ቤት አባላት ባገኙት 65 ከመቶ ድምጽ አሸንፈው የህንድ ፕሬዝዳንት መሆናቸውን አልጀዚራ ዘገበ ፡፡ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ቃለ መሃላ ሲፈጽሙ እንደተናገሩት ህንድ ውስጥ ገለልተኛና የመጨረሻ ድሆች የሆኑት 2 መቶ ሚሊዮን የዳሊት ማህበረሰብ አባላት... More

ባህር ዳር፡ ሐምሌ 18 /2009 ዓ/ም (አብመድ)ኬንያ ቀደም ብላ ከታንዛኒያ በሚገቡ የስንዴ ዱቄት እና የጋዝ ምርት ላይ እገዳዎች አድርጋ የቆየች ስትሆን ታንዛኒያም በበኩሏ አግዳ የቆየችውን የኬኒያን የወተት እና ሌሎች ሸቀጦች እገዳ ለማንሳት ሁለቱም ሃገራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ዴይሊ ኔሽን ዘገበ፡፡

ባህር ዳር፡ ሐምሌ 18 /2009 ዓ/ም (አብመድ)የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ )ከፍተኛ አመራሮች በቀጣናው ውስጥ የወሊድ ምጣኔን ለመቀነስ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የቀጣናው የሕዝብ ብዛት ከሚጠበቀው በላይ እያሻቀበ ነው የሚሉት አመራሮች ቁጥሩ በዚህ መጠን የሚቀጥል ከሆነ አስቸጋሪ ይሆናል ብለዋል ፡፡

ባህር ዳር፡ ሐምሌ 17 /2009 ዓ/ም (አብመድ) በሱዳን ገዳሪፍ እና በአማራ አዋሳኝ ግዛቶች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የሱዳን የህግ አውጭ ቡድን በዚህ ሳምንት ወደ አማራ ክልል በማቅናት የልምድ ልውውጥ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡
ከሐምሌ 19 እስከ ሓምሌ 23 2009 ዓ.ም... More

ባህር ዳር፡ ሐምሌ 17 /2009 ዓ/ም (አብመድ) በህመም ምክኒያት ሃገራቸውን ለቀው ከወጡ በኋላ ያሉበት ሁኔታ እያነጋገረ የቆየው የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ለንደን ውስጥ በደህና ሁኔታ ላይ መኖራቸውን ቢቢሲ ዘገበ ፡፡

ባህር ዳር፡ ሀምሌ 16 /2009 ዓ/ም (አብመድ)የአፍሪካ ህብረት የጋራ ፓስፖርትን ተግባራዊ ለማድረግ ሂደቱ ያለበትን ደረጃ በመገምገም ሁሉም አባል አገሮች ለተግባራዊነቱ መረባረብ እና መግባባት እንደሚገባቸው ተገለጸ ፡፡
የጋራ ፓስፖርቱ አሁን ያሉትን ነባር ፓስፖርቶች ለመተካት የሚያስችል ሲሆን የ 55ቱ አባል አገራት ዜጎች በመላው አህጉሪቱ ለመንቀሳቀስ በሚፈልጉበት ወቅት የቪዛ ክፍያ ቅናሽ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡

Pages

Video News

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች ፈጣንና ሁሉን አውዳሚ ተምች በመከላከል አርአያነታቸውን አሳይተዋል
በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች ፈጣንና ሁሉን አውዳሚ ተምች በመከላከል አርአያነታቸውን አሳይተዋል
ጐንጅ ቆለላ እና በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጃዊ ወረዳዎች ፈጣንና ሁሉን አውዳሚ ተምችን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ጐንጅ ቆለላ እና በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጃዊ ወረዳዎች ፈጣንና ሁሉን አውዳሚ ተምችን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

Amharan News

Ethiopian News

Visitors

  • Total Visitors: 1812903
  • Unique Visitors: 113904
  • Published Nodes: 1864
  • Since: 03/23/2016 - 08:03