Latest News

ባህርዳር፡ታህሳስ 20/2010 ዓ/ም(አብመድ)ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚህ ኔታንያሁ የእስራኤልን ህልውና ለመፈታተን   ሙከራየሚያደርጉትን ሁሉ መከላከያቸው በአየር፣በባህርም ሆነ በየብስመመከትየሚያስችልቴክኖሎጂና ብቃት እንዳለው በአየር ሃይል የምረቃ በዓል ላይ መናገራቸውን ዢንዋ ዘገበ ፡፡

ባህርዳር፡ታህሳስ 20/2010 ዓ/ም(አብመድ)የተባበሩት መንግስታትድርጅት ባሳለፍነው ሳምንት የዓለም ሀገራት ከሰሜን ኮሪያ ጋርያላቸውን የንግድ ግንኙነት እንዲያቆሙጥብቅማዕቀብቢጥልም ቻይና ግን በድብቅ ነዳጅ እንደምታቀርብላት ደቡብ ኮሪያ አጋለጠች፡፡

ባህርዳር፡ታህሳስ 20/2010 ዓ/ም(አብመድ)ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምዕራብ አፍሪካዊቷ ናይጄሪያ ከጂሃዲስቱ የሽብር ቡድን ቦኮ ሃራም ጋር የምታደረገውን ትግል በመደገፍ ሱፐር ቱካኖ ኤ 29 የተባሉ 12 ተዋጊ አውሮፕላኖችን እና የጦር መሳሪያዎችን ለመሸጥ መወሰናቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

ባህርዳር፡ታህሳስ 20/2010 ዓ/ም(አብመድ)ሶማሊያ ከ27 ዓመት በኋላ የአየር ክልሏን መቆጣጠር መጀመሯን ፕሬዝዳንት መሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ተናገሩ፡፡

በሞቃዲሾ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ የተገነቡ ቢሮዎችን እና መሳሪያዎችን በይፋ መርቀው የከፈቱት ፕሬዝዳንት ፋርማጆ ሶማሊያ የአየር ክልሏን መቆጣጠሯ ለሃገሪቱ እድገት አንድ እርምጃ ነው ብለውታል፡፡

ባህርዳር፡ታህሳስ 20/2010 ዓ/ም(አብመድ)በላይቤሪያ ምርጫ ጆርጅ ዊሃ ማሸነፉን ተከትሎ ዋና ከተማዋ ሞንሮቭያ በደጋፊዎቹ ጭፈራ ደምቃ መታየቷን ቢቢሲ አስነብቧል፡፡

የቀድሞውየእግርኳስኮከብጆርጅ ዊሃየላይቤሪያፕሬዝዳንትሆኖመመረጡ ለውጥ ለናፈቃቸው ላይቤሪያውያን ተስፋ ማምጣቱን አደባባይ የወጡ ደጋፊዎቹ ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ማክሰኞ ዕለት በተካሄደው ብሄራዊ ምርጫ ጆርጅ ዊሃ የመራጮችን 60 በመቶ ድምጽ በማግኘት በፖለቲካው ዘርፍ ረጅም ልምድ ያካበቱ ተቀናቃኙን ጆሴፍ ቡአካይን አሸንፏቸዋል፡፡

ባህርዳር፡ታህሳስ19/2010 ዓ/ም(አብመድ)በባራክ ኦባማ አስተዳደርእስራኤልእናአሜሪካአጋጥሟቸው የነበረውን አንፃራዊየሆነ የግንኙነትመሻከርፕሬዝዳንት ዶናልድትራምፕ ኢየሩሳሌምን ለዋና ከተማነት በመሰየማቸው ምክኒያት ወደጦፈ ወዳጅነት መሸጋገሩን ቢቢሲ ዘግቧል ፡፡   Donald Trump places his hand on the Western Wall in Jerusalem on 22 May 2017

ባህርዳር፡ታህሳስ19/2010 ዓ/ም(አብመድ)አንድ ከፍተኛ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣን ሶማሊያ ለፌደራል በጀት ያጸደቀችው 274 ሚሊዮን ዶላር ለኢኮኖሚ ልማት እንዲውል መታቀዱ የሚያበረታታ ነው ማለታቸውን ሮይተርስ ዘገበ፡፡

የአፍሪካ ቀንድ ሃገራት የልማት እንቅስቃሴ ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት አንድ እርምጃ እየተራመዱ መሆኑ ነው የሚነገረው፡፡

ባህርዳር፡ታህሳስ19/2010 ዓ/ም(አብመድ)በትናንትናው ዕለት አንጎሳት - 1 የተባለች የአንጎላ የቴሌኮሙኒኬሽን  ሳተላይት ካዛክስታን ከሚገኘው ባይኮኑር  የሮኬት ማስወንጨፊያ ጣቢያ ወደጠፈር የመምጠቋን መረጃ ማድረሳችን የሚታወስ ነው ፡፡

ይሁን እንጂ ሳተላይቷ ወደጠፈር በመጠቀች በአንድ ቀን ልዩነት ውስጥ ከግንኙነት ውጪ መሆኗን የሩሲያ ጠፈር ኤጀንሲ ማስታወቁን ታዝ የዜና ወኪልን ጠቅሶ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል ፡፡ 

ባህርዳር፡ታህሳስ19/2010 ዓ/ም(አብመድ)የሁለት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ ሱዳን የገቡት የኳታር ጦር አዛዥ ጄኔራል ጋኒም ቢን አል-ጋኒም
... More

ባህርዳር፡ታህሳስ19/2010 ዓ/ም(አብመድ)አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ  4 የማሰልጠኛ ማዕከላት አሉት፡፡ደብረ ብርሃን ፣ሀገረማሪያም፣ማይጨው እና በቆጂ ናቸው፡፡በዛሬው ዕለትም አዲሱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የደብረ ብርሃን አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ተቋምን ጎብኝቷል፡፡No automatic alt text available.

Pages

Video News

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች ፈጣንና ሁሉን አውዳሚ ተምች በመከላከል አርአያነታቸውን አሳይተዋል
በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች ፈጣንና ሁሉን አውዳሚ ተምች በመከላከል አርአያነታቸውን አሳይተዋል
ጐንጅ ቆለላ እና በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጃዊ ወረዳዎች ፈጣንና ሁሉን አውዳሚ ተምችን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ጐንጅ ቆለላ እና በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጃዊ ወረዳዎች ፈጣንና ሁሉን አውዳሚ ተምችን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

Amharan News

Ethiopian News

Visitors

  • Total Visitors: 2827120
  • Unique Visitors: 179002
  • Published Nodes: 2512
  • Since: 03/23/2016 - 08:03