Latest News

ባህር ዳር፡ ሐምሌ 24/2009 ዓ/ም (አብመድ)የገዳሪፍ ምክር ቤት ከአማራ ክልል ምክር ቤት ጋር በጸጥታ ጉዳዮች፣በንግድ ልውውጦች፣በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርና በባህር ትስስር ዙሪያ የልምድ ልውውጥ በማድረግ በቀጣይ በምን ስራዎች ላይ ማተኮር እንዳለባቸው  በባህር ዳር ተወያይተዋል፡፡

ባህር ዳር፡ ሐምሌ 24/2009 ዓ/ም (አብመድ)ፐሬዝዳንት ፑቲን ትዕዛዙን ያሳለፉት በሩሲያ የአሜሪካ ኢምባሲ ላይ ያሉት  1ሺህ ዲፕሎማቶች   ቁጥራቸው ከፍተኛ በመሆኑ ነው ተብሏል፡፡ምንም እንኳን ቁጥራቸው ከፍተኛ ነው ይባል እንጂ ሀገሪቱ ከዲፕሎማቲክ ስራቸው ውጭ የስለላ ስራ ይሰራሉ ብላ ስለምትጠረጥር ነው የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡

 

ከዚህ በተጨማሪ ግን የፕሬዝዳንትቱ ቀጥተኛ ትዕዛዝ የአሜሪካ ሴኔት አርብ ዕለት በሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል ረቂቅ በማዘጋጀቱ አጸፋ ነው ተብሏል፡፡

 

ባህር ዳር፡ ሐምሌ 24/2009 ዓ/ም (አብመድ)12 ሺ እግረኛ ጦር፣ 7 መቶ ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎች ፣ሚሳይሎችና ተዋጊ ጄቶች በተሳተፉበት ወታደራዊ ትርዒት ላይ የተገኙት የቻይና ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ የሃገሪቱ ጦር ሃይል ‹ የትኛውንም ወራሪ ጠላት የመደምሰስ አቅም እንዳለው › መናገራቸውን ስካይ ኒውስ ዘግቧል ፡፡... More

ባህር ዳር፡ ሐምሌ 23/2009 ዓ/ም (አብመድ)ኢንዶራማ ኤሌሜ ማዳበሪያ እና ኬሚካል ሃላፊነቱ የተወሰነ ኩባንያ ሃርኮርት በተባለው የሃገሪቱ ወደብ ላይ በ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ያስገነባው ዘመናዊ የማዳበሪያ ማምረቻ ተቋም በናይጄሪያ ምክትልና ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዬሚ ኦሲንባጆ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን ፐሪሚየም ታይምስ ዘገበ ፡፡

ባህር ዳር፡ ሐምሌ 23/2009 ዓ/ም (አብመድ)በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ሰብአዊ ወንጀል እየፈጸመ የሚገኘው አማጺ ቡድን መሥራችና መሪ የሆነው ንታቦ ንታቤሪ ሼካ በኮንጎ ለተሠማራው የተባበሩት መንግስታት ጦር እጁን መስጠቱን ሮይተርስ ዘገበ ፡፡

ባህር ዳር፡ ሐምሌ 23/2009 ዓ/ም (አብመድ)
የከተማው ፖሊስ ጽ/ቤት ሀላፊ ኢንስፔክተር መባቻው ክብረት በነዋሪዎች ለተነሱት የጸጥታ ችግሮች እንዳሉት ወጣቱ ጀርባው ይጠና ተብሎ የታሰረም የተሰቃየም የለም ፡፡መገለጫ የለውም ፤ግለሰቦችን ይዘን አላሰርንም ብለዋል፡፡

ባህር ዳር፡ ሐምሌ 22 /2009 ዓ/ም (አብመድ)በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ተሳትፈው የተገኙ 227 ግለሰቦች እያንዳንዳቸው እስከ 20 ዓመት በሚደረስ ጽኑ እስራት መቀጣታቸውን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታውቋል።

ባህር ዳር፡ ሐምሌ 22 /2009 ዓ/ም (አብመድ)በትናትናው ዕለት በሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ ሞሰቢት አካባቢ መንገድ የሳተው አይሱዙ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በሁለት ሰዎች ላይ ከፍተኛ አደጋ ፤ በቀሪዎቹ ላይ ቀላል አደጋ መድረሱን የቡግና ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡... More

ባህር ዳር፡ ሐምሌ 22/2009 ዓ/ም (አብመድ)የአውሮፓ ህብረት በእቅዱ ውስጥ 53 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ለአፍሪካ በመስጠት የሊቢያን ድንበር  በመጠበቅ ሜዲትራኒያንን አቋርጠው አውሮፓ የሚደርሱትን ስደተኞች መቆጣጠር የሚያስችል እቅድ ነው ያወጣው፡፡

እቅዱን ይፋ ያደረገው የአውሮፓ ህብረት እንዳለው አብዛኛው ስደተኛ የሚመጣው በሊቢያ  በኩል  ነው፡፡ ጣሊያን የሚደርሱትን ለማስቆም ደግሞ የአውሮፓ ህብረት አንድ እርምጃ ወደፊት መራመድ ይጠበቅበታል፡፡ ለዚህም ነው ይህን እቅድ ይፋ ያደረግነው ብሏል፡፡

ባህር ዳር፡ ሐምሌ 21 /2009 ዓ/ም (አብመድ)የቱርክ የዜና አቅራቢ ኤጀንሲ አናዶሉ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ በመፍጠር ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የኢፌዲሪ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዶክተር ነገሬ ሌንጮ መናገራቸውን አናዶሉ ዘገበ ፡፡
... More

Pages

Video News

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች ፈጣንና ሁሉን አውዳሚ ተምች በመከላከል አርአያነታቸውን አሳይተዋል
በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች ፈጣንና ሁሉን አውዳሚ ተምች በመከላከል አርአያነታቸውን አሳይተዋል
ጐንጅ ቆለላ እና በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጃዊ ወረዳዎች ፈጣንና ሁሉን አውዳሚ ተምችን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ጐንጅ ቆለላ እና በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጃዊ ወረዳዎች ፈጣንና ሁሉን አውዳሚ ተምችን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

Amharan News

Ethiopian News

Visitors

  • Total Visitors: 1813169
  • Unique Visitors: 113918
  • Published Nodes: 1864
  • Since: 03/23/2016 - 08:03