Latest News

ባህር ዳር፡ መስከረም 9 /2010 ዓ/ም (አብመድ)ቀድም ብሎ የካረቢያን ደሴቶችን  የመታው ሄሪከን ማሪያ  ዶሚኒካ ሪፓብሊክን አጥቅቷል፡፡ከዶሚኒካ በመነሳትም የአሜሪካዋን ፖርቶሪኮን አጥቅቷል፡፡በአውዳሚነቱ እጅጉን ከእስከዛሬዎቹ ጉዳቶች  የባሰ ነው የተባለው ሀሪከን ማሪያ  ዶሚኒካ ላይ አጥፊነቱ የባሰ ነው ይላል የሲኤንኤን ዘገባ፡፡

የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ሮስቬልት ስከሪትን ጠቅሶ እንደዘገበውም ዶሚኒካ ምንም የተረፋት መሰረተ ልማት እንደሌለ ተነግሯል፡፡

ባህር ዳር፡ መስከረም 9 /2010 ዓ/ም (አብመድ ) በሰሜናዊ ምስራቅ ናይጄሪያ በጋዜጠኝነት ሙያ የተሠማራችው አሚና ዩጉዳ ለሶስተኛ ጊዜ የተካሄደውን የቢቢሲ ዓለም አቀፍ ውድድር በማሸነፍ የኮምላ ዱሞር ሽልማት መቀበሏን ቢቢሲ ዘግቧል ፡፡ 
በናይጄሪያ የጎቴል ቴሌቪዥን የዜና አንባቢ... More

ባህር ዳር፡ መስከረም 9 /2010 ዓ/ም (አብመድ ) የዚምባቡዌ መንግስት የአልኮል ሽያጭን የሚገድብ ህግ ያጸደቀ ሲሆን በህጉ ውስጥ ለነፍሰጡር ሴቶች አልኮል መሸጥ በህግ እንደሚያስቀጣ አመላክቷል ፡፡
በሃገሪቱ የሚታተም ጋዜጣ እንደዘገበው የአልኮል መጠጥ መጠንን ከ 0.08 ሚሊ ሊትር በላይ ጠጥቶ የተገኘ አሽከርካሪ አስፈላጊው የህግ እርምጃ እንደሚወሰድበት ዘግቧል፡፡

ባህር ዳር፡ መስከረም 9 /2010 ዓ/ም (አብመድ ) ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ በመንግስታቱ ድርጅት መዋቅር ማሻሻያ ዙሪያ ትናንት በተደረገ የከፍተኛ ደረጃ ምክክር ተሳትፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ“ፆታዊ ጥቃትና ብዝበዛን ለማስቆም ልዩ እርምጃዎች” በሚል መሪ ቃል በተደረገ ውይይት... More

ባህር ዳር፡ መስከረም 8/2010 ዓ/ም (አብመድ)የእምቦጭ አረምን በሰው ጉልበት የማስወገድ ዘዴ ተመራጭ ቢሆንም አረሙ ከተወገደ በኋላ አቀማመጥ ላይ ጥንቃቄ ካልተደገ የአረሙ መስፋፋት እንደሚቀጥል በአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲዩት የባህር ዳር ዓሳና ሌሎች ው/አ/ም/ ማዕከል ዳይሬክተር ተመራማሪ ተናግረዋል፡፡

ባህር ዳር፡ መስከረም 8 /2010 ዓ/ም (አብመድ)የዓለም ሃገራትን ስጋት ወደጎን በመግፋት የኒውክሌር ባለቤት ለመሆን እየተጣደፈች የምትገኘው ሰሜን ኮሪያ ተደጋጋሚ የሚሳይል ሙከራ እያደረገች ባለችበት ባሁኑ ወቅት እና የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ በሚጀመርበት ዋዜማ ላይ ቻይና እና ሩሲያ በሰሜን ኮሪያ ድንበር አቅራቢያ የባህር ላይ ወታደራዊ ልምምድ መጀመራቸውን ሮይተርስ ዘገበ ፡፡

ባህር ዳር፡ መስከረም 8/2010 ዓ/ም (አብመድ)የአፍሪካውያንን የግብርና ተሞክሮ በማሻሻል ያለውን የምግብ ክፍተት ለመሙላት የተሻለ ስራ ለሚያከናወኑ አፍሪካውያን የሚሰጠው የዚህ ዓመት ሽልማት ለኬንያዊቷ ፕሮፌሰር ሩት ኦኒያንጎ እና ለማሊዋ ስራ ፈጣሪ ማይሞና ሲዲቤ ኩሊባሊ መሠጠቱን አፍሪካ ኒውስ ዘገበ ፡፡

ባህር ዳር፡ መስከረም 7/2010 ዓ/ም (አብመድ )ኢትዮጵያ እና ኬንያ አፍሪካዊያኑን ባለግዙፍ ኢኮኖሚ ሃገራት ናይጄሪያን ፣ደቡብ አፍሪካን እና ግብጽን በመብለጥ በኢንቨስትመንት ፉክክሩ የተሻለ ውጤት ሊያስመዘግቡ እንደሚችሉ ዓለምኣቀፉ የስጋት አማካሪ ተቋም ኮንትሮል ሪስክ ሪፖርት ማድረጉን ዢንዋ ዘግቧል፡፡ 

ባህር ዳር፡ መስከረም 7/2010 ዓ/ም (አብመድ )የቀድሞው የግብጽ ፕሬዝዳንት ሙሀመድ ሙርሲ የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ መሪ ሆነው በምርጫ ስልጣን ላይ ቢወጡም መሪ እያሉ ለኳታር ይሰልሉ ነበር በማለት የግብጽ ፍርድ ቤት ትናንት የ25 ዓመት እስራት ፈርዶባቸዋል፡፡

ባህር ዳር፡ መስከረም 7/2010 ዓ/ም (አብመድ )በደቡብ ወሎ ዞን በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተሰማሩ ወጣቶች 98 ሚሊዮን ብር የሚገመት አስተዋፅኦ ማድረጋቸውን የዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ፡፡

           በመምሪያው የወጣት ማደራጃና ንቅናቄ ተሳትፎ የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ምስጋናው ደምሴ በበጐ ፈቃድ አገልግሎቱ ከ4 መቶ 89 ሺህ በላይ የሚሆኑ ወጣቶች በተለያዩ ስራዎች ተሳትፎ አድርገዋል ብለዋል፡፡

Pages

Video News

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች ፈጣንና ሁሉን አውዳሚ ተምች በመከላከል አርአያነታቸውን አሳይተዋል
በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች ፈጣንና ሁሉን አውዳሚ ተምች በመከላከል አርአያነታቸውን አሳይተዋል
ጐንጅ ቆለላ እና በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጃዊ ወረዳዎች ፈጣንና ሁሉን አውዳሚ ተምችን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ጐንጅ ቆለላ እና በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጃዊ ወረዳዎች ፈጣንና ሁሉን አውዳሚ ተምችን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

Amharan News

Ethiopian News

Visitors

  • Total Visitors: 2064093
  • Unique Visitors: 126453
  • Published Nodes: 2015
  • Since: 03/23/2016 - 08:03