Latest News

ባህር ዳር፡ ጥቅምት 8/2010 ዓ/ም (አብመድ)በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የተካሄደው ጉብኝት ኢትዮጵያ በግድቡ ግንባታ ያላትን ግልጸኝነት የሚያሳይ መሆኑን የሱዳንና የግብፅ የውሃና መስኖ ሚኒስትሮች ገለጹ።

የኢትዮጵያ፣የግብፅና የሱዳን ውሃ ሚኒስትሮች ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዋናውን ግድብ ጨምሮ የኮትቻ ግድብ እና የውሃ ማስተንፈሻ ግንባታዎችን ትናንት ጎብኝተዋል።

ባህር ዳር፡ ጥቅምት 8/2010 ዓ/ም (አብመድ)የኢትዮጵያን ቡና ባህላዊና ማህበራዊ እሴት ለዓለም ለማስተዋወቅ ያለመ የቡና ዓውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ሊዘጋጅ ነው።

አውደ ርዕዩ ከየካቲት 6 እስከ 11 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል።

ባህር ዳር፡ ጥቅምት 8/2010 ዓ/ም (አብመድ)ትምህርትና ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጤናማ እና የተማረ ዜጋ በጋራ ማፍራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።

ባህር ዳር፡ ጥቅምት 8/2010 ዓ/ም (አብመድ)የቱኒዚያ መንግስት የሰርጎ ገብ ጥቃቶችን የመከላከል አቅም እንዳለው በማሳየቱ እና ሰላም ማምጣት በመቻሉ እ.ኤ.አ.በ2017 ሃገሪቱን የጎበኙ የውጭ ሃገር ቱሪስቶች ቁጥር በያዝነው ዓመት 24 በመቶ ማደጉን ባለስልጣናቱ ለሮይተርስ አስረድተዋል፡፡

ባህር ዳር፡ ጥቅምት 7/2010 ዓ/ም (አብመድ)አቶ በረከት ስምኦን በፈቃዳቸው ለመልቀቅ ጥያቄ ማስገባታቸውን የመንግስት ኮምንኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡በሚኒስትር ማዕረግ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙት አቶ በረከት ስምኦን ከሀላፊነታቸው ለመነሳት ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ደብዳቤ አስገብተዋል ብለዋል።
... More

ባህር ዳር፡ ጥቅምት 7/2010 ዓ/ም (አብመድ)የውሃ መስኖና ኤሌትሪክ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ብዙነህ ቶልቻ ለኢዜአ እንደገለጹት ለአንድ ቀን በሚካሄደው የሶስትዮሽ ስብሰባ ላይ የሶስቱ አገራት የውሃ ሚኒስትሮች፤ ዲፕሎማቶች፤ ምሁራንና የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ይሳተፋሉ።

ባህር ዳር፡ ጥቅምት 7/2010 ዓ/ም (አብመድ)የኢትዮጵያ፣ሱዳንና ግብጽ የውሃ፣መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትሮች የህዳሴውን ግድብ በመጎብኘት ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ ውሃ፣መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ፣የሱዳኑ አቻቸው ሙአተዝ ሙሳ እና የግብጹ ውሃ ሃብትና መስኖ ሚኒስትሩ መሃመድ አብደል አቲ በጉባ ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በመጎብኘት ላይ ናቸው።

ባህር ዳር፡ ጥቅምት 7/2010 ዓ/ም (አብመድ)የራስ ግንብ ሙዚየም በፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አነሳሽነት በ2003 ዓ.ም በጎንደርና በቪንስስ ከተማ ትብብር ተጀምሯል፡፡ 
የራስ ግንብ ጥገና በሁለቱ እህትማማች ከተሞች ትብብር ከተከናወነ በኋላ ወደ ታሪካዊና ባህላዊ ሙዚየምነት የመቀየር ስነ ስርዓት ተካሂዷል፡፡ 

ዕለቱ ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በላቀ ቁርጠኝነት ለማጠናቀቅ ቃል የሚገባበት ነው 

 

ባህር ዳር፡ ጥቅምት 7/2010 ዓ/ም (አብመድ)የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት /ዩ.ኤስ.አይ.ዲ/ የእናቶችና ሕጻናትን ሞት ለመቀነስ በ181 ሚሊዮን ዶላር የሚተገበሩ አራት መርሃ ግብሮችን ይፋ አደረገ።

Pages

Video News

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች ፈጣንና ሁሉን አውዳሚ ተምች በመከላከል አርአያነታቸውን አሳይተዋል
በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች ፈጣንና ሁሉን አውዳሚ ተምች በመከላከል አርአያነታቸውን አሳይተዋል
ጐንጅ ቆለላ እና በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጃዊ ወረዳዎች ፈጣንና ሁሉን አውዳሚ ተምችን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ጐንጅ ቆለላ እና በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጃዊ ወረዳዎች ፈጣንና ሁሉን አውዳሚ ተምችን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

Amharan News

Ethiopian News

Visitors

  • Total Visitors: 2296062
  • Unique Visitors: 136060
  • Published Nodes: 2118
  • Since: 03/23/2016 - 08:03