26ኛው የግንቦት 20 በዓል በክልሉ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል- የአማራ ክልል ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

ባህር ዳር፡ ግንቦት 15/2009 ዓ/ም(አብመድ)የአማራ ክልል ኮምንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሪክተር አቶ ንጉሱ ጥላሁን በሰጡት መግለጫ የዘንደሮውን በዓል በክልል ደረጃ ስናከብር ፡አንደኛ የህዝቦች እኩልነት ፣ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ስርዓት በመገንባት ሂደት በ26 አመቱ ሂደት ውስጥ ክልላችን የተጓዘበት ጉዞ የምናይበት ነው፡፡ወቅቱ የወለዳቸው ያሉ ተግዳሮቶችና ችግሮችን ለመሻገር የምንመክርበት ፣የምንወያይበት ከዚህም ተነስተን ትምህርት የምንወስድበትና አቅጣጫ የምናስቀምጥበነው ብለዋል፡፡

አቶ ንጉሱ አክለውም በክልል ደረጃ በዋና ዋና ከተሞቻችን ምሁራንን፣ነዋሪዎችን፣ወጣቱን እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያሳተፉ የውይይት መድረኮች ይኖራሉ፡፡የፓናል ውይይቶችና መድረኮች በየአካባቢው አድማሳዊ ሳይሆን ከባቢያዊ የሆኑ መመማሪያ መድረኮች የሚሆኑበት ምሁራዊ ሀሳቦች የመሰጥበት፣በችግሮችና ሴኬቶች  ላይም ምሁራዊ ትንታኔ የሚሰጥበትና ሰው የመሰለውን ሀሳብ አራምዶ ለለውጥ ሀሳብ የሚለዋወጥባቸው መድረኮች ይሆናሉ ብለዋል፡፡

በዓሉ በስፖርት ፣በኪነ-ጥበብ ፣በኢግዙቪሽን ና ሌሎች መሰናዶዎች አማካኝነት ይከበራል፡፡

          የህዝቦች እኩልነትና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጠ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እየገነባች ያለች ሃገር ኢትዮጵያ በሚል መሪ መልዕክት ይከበራል፡፡

ጌታቸው አስማማው

ተጻፈ በመሰረት አስማረ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3537623
  • Unique Visitors: 199679
  • Published Nodes: 2652
  • Since: 03/23/2016 - 08:03