16ተኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ስድስተኛ ቀን ላይ ይገኛል፡፡

ባህር ዳር፡ ነሀሴ 3/2009 ዓ/ም (አብመድ)ዛሬ ምሽት 3፡05 ጀምሮ 9 የማጣሪያና የፍፃሜ ውድድሮች መርሃ ግብር ተይዞላቸዋል፡፡
ኢትዮጵያዊያን አትሌቶችም በ5000 ሜትር የወንዶች ማጣሪያ እና በ3000 ሜትር የሴቶች መሰናክል ማጣሪያቸውን ያደርጋሉ፡፡

Image may contain: one or more people, stadium and crowd
ኢትዮጵያ በ3000 ሜትር የሴቶች መሰናክል ማጣሪያ በሶፊያ አሰፋ ብርቱካን ፈንቴና እቴነሽ ዲሮ ትወከላለች፡፡
የዕለቱ የውድድር መርሃ ግብር መክፈቻ ሆኖ ምሽት 3፡05 ላይ ይጀመራል፡፡
በወንዶች 5000 ሜትር ማጣሪያ ላይ ኢትዮጵያ በ4 አትሌቶች የምትወከል ይሆናል፡፡
በርቀቱ ድንቀ ብቃት ላይ የሚገኘውን ሙክታር ኢድሪስን ጨምሮ ዮሚፋ ቀጀልቻ እና ታዳጊው አትሌት ሰለሞን ባርጋ ምሽት 4፡05 ላይ በሚደረገው ማጣሪያ ይሳተፋሉ፡፡ሀጎስ ገ/ህይወት ከጉዳቱ ባለማገገሙ ከዛሬው ማጣሪያ ውጭ ሆኗል፡፡ሀጎስ በዲያመንድ ሊግ አጠቃላይ አሸናፊ ስለነበር 4ኛ ተሰታፊ ሆኖ ለንደን መሄዱ ይታወሳል፡፡
በርቀቱ ሞፍራ የሁለተዮሽ ድል ባለቤት ለመሆን ተሳታፊ ነው፡፡
ዛሬ በጦር ውርወራ ሴቶች፣ በ400 ሜትር መሰናክል ወንዶች እና በ400 ሜትር ሴቶች የፍፃሜ ውድድሮች ይደረጋሉ፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3051222
  • Unique Visitors: 184021
  • Published Nodes: 2537
  • Since: 03/23/2016 - 08:03