ፕሬዝዳንት አዳማ ባሮው ለውጥ ለማምጣት ቃል ገቡ

ፕሬዝዳንት አዳማ ባሮው ለውጥ ለማምጣት ቃል ገቡ

ባሕር ዳር፡ ጥር 22 / 2009 ዓ.ም (አብመድ)ከጥቂት ውዝግብ በኋላ በቅርቡ ስልጣናቸውን የተረከቡት የጋምቢያው ፕሬዝዳንት አዳማ ባሮው የሃገራቸውን የደህንነት ኤጀንሲ ስም ለውጠው በአዲስ መልክ ለማዋቀርና የሚዲያ ነጻነትን ለማረጋገጥ እንደሚሰሩ ቃል መግባታቸውንጋርዲያን ዘገበ ፡፡

በትረ- መንግስታቸውን ለማደላደል ስራ ከመጀመራቸው በፊት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሰብአዊ መብቶችን በመጣስ፣ በርካታ ዜጎችን በመሰወር እና በማሰቃየት የሚታወቀው የተሰናባቹ መሪ ያህያ ጃሜህ የብሄራዊ ደህንነት ኤጀንሲን እንደገና ለማደራጀት መነሳታቸውን ተናግረዋል ፡፡

 

ምንም እንኳ 90 ከመቶው የጋምቢያ ህዝብ የእስልምና እምነት ተከታይ ቢሆንም እ.ኤ.አ. በ2015 በጃሜህ ትዕዛዝ በሃገሪቱ መጠሪያ ላይ የተጨመረውንእስላማዊ › የሚል ቃል በማውጣት ወደቀድሞው ስምዋ ‹የጋምቢያ ሪፐብሊክለመመለስ ወስነዋል ፡፡

 

ህግን ማክበር የወቅቱ ጥያቄ መሆን ይኖርበታል የሚሉት ባሮው በአጭር ቀናት ውስጥ ካቢኔ በማዋቀር ወደስራ ለመግባት እየተንቀሳቀሱ ሲሆን ተመራጮቹ ስራቸውን ከመጀመራቸው በፊት የግል ሃብታቸውን ማሳወቅ እንደሚገባቸው ተጠቅሷል ፡፡ የሃገራቸውን የፋይናንስ ደረጃ ከሚመለከተው አካል በማጣራት ለህዝባቸው ይፋ እንደሚያደርጉ የገለጹት ባሮው የፕሬስ ነጻነት ለማስፈን ጠንክረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል ፡፡

 

አሁን ጋምቢያ ውስጥ ስለሚገኙት 4 ሺ የምዕራብ አፍሪካ ወታደሮች ሁኔታ ከጋዜጠኞች የተጠየቁት ባሮው ህዝቡ እስኪረጋጋ ድረስ ደህንነትን የማስከበርና ለጦር ሃይሉ የቴክኒክ ድጋፍ የማበርከት ሚና እንደሚጫወቱ ገልጸው እስከመቼ ሊቆዩ እንደሚችሉ ከወዲሁ ለመናገር አይቻልም ብለዋል ፡፡

 

ይህ በእንዲህ እንዳለ በምክትል ፕሬዝዳንትነት እንዲያገለግሉ የተመረጡት ፋቱማታ ጃሎው ታምባጃንግ በህገመንግስቱ መሰረት እድሜያቸው በመግፋቱ ሃለፊነታቸውን በብቃት ለመወጣት ብቁ አይደሉም የሚል ትችት እየተሰነዘረ እንደሚገኝ ታውቋል ፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3527452
  • Unique Visitors: 199331
  • Published Nodes: 2627
  • Since: 03/23/2016 - 08:03