ፕሬዝዳንት ትራምፕ የ460 ቢሊዮን ዶላር የንግድ ስምምነት ከሳውዲ ጋር ተፈራረሙ

ባህር ዳር፡ ግንቦት 13/2009 ዓ/ም(አብመድ)ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከአረብ ሀገራት መሪዎች ጋር ለመምከር ወደ ሳወዲ  አምርተዋል፡፡ የመሪዎች ጉባኤ ከመጀመሩ በፊት ከሳውዳረቢያው ንጉስ  ሳልማን ቢን አብዱላዚዝ ጋር የንግድ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል፡፡

የንግድ ስምምነቱ በአጭርና በረዥም ጊዜ ተግባራዊ የሚደረግ ነው፡፡በስምምነቱ መሠረትም 110 ቢሊዮን ዶላር በአጭር ጊዜ የሚፈጸም ሲሆን ለመሳሪያ ሽያጭ እንደሚውል ሲኤንቢሲ ዘግቧል፡፡ቀሪው 350 ቢሊዮን ዶላር በቀጣይ 10 አመታት ውስጥ ተግባራዊ የሚደረግ የንግድ ስምምነት ነው፡፡

አሜሪካ እና ሳውዲአረቢያ ሽብርተኝነትን ለመግታት በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3537582
  • Unique Visitors: 199679
  • Published Nodes: 2652
  • Since: 03/23/2016 - 08:03