ጥናትና ምርምሮች የህብረተሰቡን ችግሮች መፍታት አለባቸው ፡-ር/መ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

ባህር ዳር፡ ግንቦት 14/2009 ዓ/ም(አብመድ)ጥናትና ምርምሮች የህብረተሰቡን ችግሮች መፍታት እንደሚኖርባቸው የአማራ ክልል  ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተናገሩ፡፡

በደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ጥራት ላይና በስነ-ምህዳር ቀጣይነት አተኩሮ በተካሄደው አውደጥናት የተገኙት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው‹‹ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት ብዙ ሙከራዎችን እያደረገ እንዳለ እንሰማለን፡፡ይህ ሀገራችን የጀመረችውን የእድገት ጉዞ ቀጣይነት ያለው እንዲሆን ጥልቁ መሳሪያ እውቀት ነውና የአካባቢውን ችግር በመፍታት ላይ የተመሰረተ በማህበረሰብ አገልግሎት ላይ ጠንክራችሁ እንደትገፉ›› በማለት አሳስበዋል፡፡

የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር አለማየሁ ከበደ በበኩላቸው ››እኔ እንደምረዳው ትምህርት ሰፊ ጽንሰ ሀሳብ ነው፡፡ፍልስፍናችንና አመለካከታችን ስለሚለያይ ለማስረዳት ይከብዳል፡፡የትምህርት ጥራት የሰው ልጆች የአስተሳሰብና የአመለካከት ቅርጽ በሚገባ ይቀይራል›› ብለዋል፡፡

የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ሂሩት ካሳው ቅድሚያ ትኩረት ለሚሰጣቸው ትኩረት በመስጠት የትምህርት ተቋማት ሊሰሩ ይገባል፡፡ማስተማር የምርምር አገልግሎትና የማህበረሰብ አገልግሎት የአንድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የማይነጣጠሉና አይቀሬ ተግባራት ናቸው፡፡

በመሆኑም ምሁራኑ የትምህርት ጥራት በማምጣት ሀገሪቱ ወደ ወደ እድገት ጎዳና እንደትሸጋገር ማስተማሩን በምርምር በመፈተሸ ወደ ተግባር እንዲለወጥ ማድረግ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

በዕለቱ በቀረበው ጥናት መሰረት የትምህርት ጥራት ችግር እነዲኖር ያደረገው የትምህርት አሰጣጥ ስርዓቱ የፈጠራና የግኝት ደረጃውን በሚገባ አለማካተቱ እንደ እጥረት ተነስቷል፡፡

የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ የፈጠራ ክህሎትን የሚያበረታታ የትምሀርት ስርዓት በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል፡፡ይህም ተማሪዎች ከግንዛቤ ባሻገር ወደ ፈጠራ እንዲገቡ ያግዛል ተብሏል፡፡

 

          ደብረታቦር ዮኒቨርሲቲ የእንስሳት ማዳቀያ ምርምር ጥናት ማዕከል ከፍቶ በመስራት ላይ ነው፡፡

ኪሩቤል ተሾመ

ተጻፈ በመሠረት አስማረ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3884793
  • Unique Visitors: 215543
  • Published Nodes: 2870
  • Since: 03/23/2016 - 08:03