ግንቦት 20 በቅርፅና ይዘቱ አዲስ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስርዓት በሃገሪቱ እንዲገነባ መሰረተ የጣለ ነው ፡-የኢፌዴሪ ኘሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ

ባህር ዳር፡ ግንቦት 19/2009 ዓ/ም(አብመድ)የግንቦት 20 የድል በዓል በቅርፅና ይዘቱ አዲስ አይነት የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስርዓት በሃገሪቱ እንዲገነባ መሰረተ የጣለ ነው ሲሉ የኢፌዴሪ ኘሬዝዳንትዶክተር ሙላቱ ተሾመ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡

          ኘሬዝዳንቱ 26ኛው የግንቦት 20 የድል በዓል ምክንያት በማድረግ ለኢትዮጵያ ህዝቦች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የሀገራችን ሀዝቦች ክቡራንና ክቡራን ከሁሉ አስቀድሜ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስትና በራሴ ስም የህዝቦች እኩልነት ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የተረጋገጠበት ፌዴራላዊ ስርዓት እየገነባች ያለች ሀገር ኢትዮጵያ በሚል መሪ ሀሳብ ለሚከበረው 26ኛው የግንቦት 20 በዓል እንኳን በሰላም አደረሰን ለማለት እወዳለሁ ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ አክለውም የግንቦት 20 የድል በዓል በቅርፅና ይዘቱ አዲስ አይነት የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስርዓት በሃገሪቱ እንዲገነባ መሰረቱ የተጣለበት ዕለት ነው፡፡የደርግ ውድቀትን ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ተሳትፏቸው የተረጋገጠበትን ህገ-መንግስት በፈቃዳቸው ማጽደቃቸውን ተከትሎ የዘላቂ ሰላም ብዝሃነትን ያከበረ እየጎለበተ የሚሄድ ዴሞክራሲያ ስርዓት እንዲሁም የፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት ባለቤት የምንሆንበት መደላድል ተፈጥሯል፡፡

ይህ እምርታም ሀገሪቱ ድህነትና ኋላ ቀርነትን ለማጥፋት ለተያያዘችው ጉዞ አመቺ ሁኔታን ከመፍጠር ባለፈ በአካባቢያዊ፣አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ መድረኮች ተደማጭነቷ እንዲጎለብት ማድረጉ የሁሉም ዜጎቻችን የደስታና የኩራት ምንጭ ሆኗል ነው ያሉት ፡፡

የተከበራችሁ መላው የሀገራችን ህዝቦች ክቡራትና ክቡራን ግንቦት 20 የኢትዮጵያ ህዝቦች በፍላጎታቸው ህገ-መንግስታዊ ዋስትና የሰጠውን ዴሞክራሲያዊ አንድነት እንዲገነቡና ማንነታቸውን አክብረው የጋራ ሀገራቸውን እንዲያበለጽጉም ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱን የቀድሞ ገጽታ በሁሉም መስክ ያሻሻለና የለወጠ ክስተት ነውመም ብለዋል፡፡

 

ጋሻው ፈንታሁን

ከአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

ተጻፈ በመሰረት አስማረ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3051228
  • Unique Visitors: 184021
  • Published Nodes: 2537
  • Since: 03/23/2016 - 08:03