ጂቡቲ ዘመናዊ ወደብ ገንብታ ለአገልግሎት ክፍት አደረገች፡፡

 

ባህር ዳር፡ ግንቦት 18/2009 ዓ/ም(አብመድ)ጂቡቲ  በአህጉር  ደረጃ ዋነኛ  የንግድ  ማዕከል ሆኖ  እንዲያገለግል  የታሰበውን  ዘመናዊ   ግዙፍ  ወደብ በመገንባት  ለአገልግሎት   ክፍት ማደርጓ ተዘገበ ፡፡

የዶራሌ ሁለገብ  ወደብ  የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ወደብ ከመላው አለም  የሚጓጓዙ እቃዎችን  የማስተላለፍ  አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን  እጅግ ዘመናዊ  የሚባሉ መሳሪያዎች  ስለተገጠሙለት  የአገልግሎት  አሰጣጡ ፈጣን  እንደሚሆን  ይጠበቃል  ፡፡

የጅቡቲ  ወደቦች ሊቀመንበር  እና የነጻ ቀጣና ባለስልጣን  አቡበከር  ኦማር በምረቃው ስነስርዓት ላይ ሲናገሩ፡-

 ‹‹ዋና ዋና የመሰረተ  ልማት ፕሮጀክቶችን  ለህዝባችን  በማቅረብ  ያለንን  አቅም ለዓለም  በማሳየታችን  ኩራት ይሰማናል ፤ በአህጉር ደረጃ  የተራቀቀ ቴክኖሎጂ ባለቤት በመሆናችን ደስተኛ ብንሆንም ከዚህ የበለጠ  ለመዘመን ጠንክረን  እንሰራለን  ››ብለዋል ፡፡

እ.ኤ.አ. በ2015  የተጀመረው የዶራሌ  ሁለገብ  ወደብ በ690 ሄክታር መሬት ላይ የሰፈረ ሲሆን  ከ 590 ሚሊዮን  ዶላር  በላይ ወጪ  ተደርጎበታል ፡፡ወደቡ ከአገልግሎት መስጫ ሥፍራዎች በተጨ ማሪም  በቂ መዝናኛዎችም  ተካተውበታል  ፡፡

ወደቡ 30ሺ መርከቦች  በዓመት የማስተናገድ  አቅም ሲኖረው  59 በመቶ ከእስያ ፣ 21 በመቶ  ከአውሮፓ  እና 16 በመቶ ከአፍሪካ ሃገሮች ዕቃዎች  የማስተላለፍ  አገልግሎት  እንደሚሰጥ  የወደቡ  ሊቀመንበር ተናግረዋል፡፡

ጅቡቲ  በዓለም አቀፉ የባህር ንግድ መስመር አቅራቢያ የምትገኝ  መሆኗ አፍሪካን  ከእስያና  ከአውሮፓ ጋር የምታገናኝ  ሁነኛ ቦታ ሆናለች ፡፡ በዓለም  በከፍተኛ  ፍጥነት  እያደጉ ካሉት  የባህር  በሮችም  አንዷ ነች ፡፡

 

ምንጭ፡-ሲ ጂ ቲ ኤን

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3300999
  • Unique Visitors: 189355
  • Published Nodes: 2588
  • Since: 03/23/2016 - 08:03