ዶናልድ ትራምፕ እስራኤልን እየጎበኙ ነው

 

ባህር ዳር፡ ግንቦት 14/2009 ዓ/ም(አብመድ)የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በመጀመሪያ የሀገራት ጉብኝታቸው ሳውዲን ጎብኝተው እግረ መንገዳቸውንም የአረብ ሀገራት መሪዎች ጉባኤ ላይ ተገኝተው ሽብርተኝነትን በጋራ ለመከላከል የአረብ ሀገራት በአንድ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የሳውዲ ቆይታቸውን አጠናቀው ዛሬ እስራኤል ገብተዋል፡፡አሜሪካ እና እስራኤል በንግድ ዘርፍ በጋራ እንዲሰሩ መንገድ ለመቀየስ እንደተገኙ እየተነገረ ነው፡፡

ትራምፕ እስራኤልና ፍልስጤም በጋራ ቁጭ ብለው ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡በቀጣይም ከሁለቱ ሀገራት መሪዎች ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው በመጀመሪያ ቆይታቸው  እስራኤልንና የፍልስጤምን ደንበር ጎብኝተዋል፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3161840
  • Unique Visitors: 186711
  • Published Nodes: 2579
  • Since: 03/23/2016 - 08:03