የፕሬዝዳንት ትራምፕ እና የሮማው ፖፕ ፍራንሲስ የሁለትዮሽ ውይይት ትኩረት ስቧል፡፡

ባህር ዳር፡ ግንቦት 16/2009 ዓ/ም(አብመድ)ከሳውዲ አረቢያ  ጀምረው  እስራኤልና  ፍልስጤምን  አካለው  ጣልያን የገቡት  የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሮም ቆይታቸው ከሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር  ከሚያደርጉት  ግንኙነት በላይ  ከፖፕ ፍራንሲስ ጋር በቫቲካን  የሚያደርጉት  ውይይት ትኩረት  መሳቡን  ቢቢሲን  ጨምሮ የተለያዩ  የመረጃ ምንጮች እየዘገቡ ነው ፡፡
Image result for pope francis and trump
 
ፕሬዝዳንት ዶናልድ  ትራምፕ  ከምርጫ  ዘመቻቸው ጀምረው  በሜክሲኮ የድንበር  አጥር ዙሪያ እና በስደተኞች  ጉዳይ የሚያራምዱትን  አቋም  ፖፕ ፍራንሲስ  በመቃወም  "ሀገራት  እንዲገናኙ  ድልድይ የሚሰራ እንጂ ፤አጥር  ገንብቶ  ግንኙነትን  የሚያራርቅ  መሪ ዓለም አትፈልግም ›› ብለው ነበር፡፡ትራምፕም  "የጳጳሱን  አስተያየት  አልቀበልም፤ከሜክሲኮ ጋር በመወገን  የተሠነዘረ ተራ ትችት ነው ›› ሲሉ ማጣጣላቸው የሚታወስ ነው ፡፡ 
 
 ትራምፕ ይዘው የተነሱትን  አቋም  አለዝበው  ከሙስሊም  ሀገራት ጋር ጤናማ  ግንኙነት  ለመፍጠር እንደሞከሩት  ሁሉ  ከ 1.2 ቢሊየን  በላይ ተከታይ ካላት የካቶሊክ  ቤተክርስቲያን  መሪ ፖፕ  ፍራንሲስ ጋር የሚያደርጉት  ውይይትም  አዲስ ምዕራፍ  ይከፍታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በተለይም  በስደተኞች  እና  በአሸባሪዎች ድርጊት ጉዳይ  የጋራ  አመለካከት  ይይዛሉ ተብሉ ይጠበቃል፡፡
ቫቲካን  በፖፕ  ፍራንሲስ  አማካኝነት  የስደተኞችን  ማህበራዊ  ቀውስ  በተመለከተ  በተለያየ  ጊዜ ዓለም ትኩረት  እንዲሰጠው ስታሳስብ  ቆይታለች ፡፡
 
ምንጭ፡-ቢቢሲ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3537588
  • Unique Visitors: 199679
  • Published Nodes: 2652
  • Since: 03/23/2016 - 08:03