የፌስቱላን ችግር ለመከላከል የሁሉም ርብርብ እንዲኖር ጤና ጥበቃ ቢሮ ጠየቀ-በክልሉ ከ38 ሺህ በላይ ሴቶች በዓመት ተጋላጭ ናቸው

ባህር ዳር፡ ግንቦት 15/2009 ዓ/ም(አብመድ)በዓለም ላይ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ እናቶች የፌስቱላ ጤና ችግር ይገጥማቸዋል፡፡በኢትዮጵያም 36ሺህ የሚጠጉ እናቶች የዚህ ችግር ተጋላጮች ናቸው፡፡

 

በየዓመቱም ከ3 ሺህ በላይ እናቶች የዚህ ሰላባ ይሆናሉ፡፡95 ከመቶ የበሽታው መንስኤ የተራዘመ ምጥና የተቀረቀረ ምጥ ናቸው፡፡ተጠቂዎቹም እስከ 4 ቀን ያምጣሉ ያሉት በባህር ዳር የሀምሊን ሆስፒታል የጽንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ቢተው አበበ ናቸው፡፡ከተቋቋመ 12 አመት የሆነው ሀምሊን የፌስቱላ ሆስፒታል በዓመት ከ2 ሺህ በላይ ለሆኑ የበሽታው ተጠቂዎች የቀዶ ህክምና አገልግሎት ይሰጣል፡፡

መቀሌ፣ይርጋለም፣ ሀረርና መቱ ላይ የፌስቱላ ማዕከላት ተከፍተው አገልግሎት እየሰጡ ነው፡፡

                    የችግሩ ተጠቂ ሆነው የዳኑ እናቶችም ህክምና ያላገኙ እናቶችን ወደ ህክምና ማዕከል ለማምጣት ኃላፊነት ይዘው ለመስራት ቃል ገብተዋል፡፡

የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ታሪኩ በላቸው እንዳሉትም የእናቶችን ጤና ለማሻሻል የጤና ተቋምትን በየአካባቢው ለመክፈት እየተሰራ ነው በቀጣይም ሙሉ ለሙሉ ችሩን ለመቅረፍ ሁሉም አካላት በርብርብ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የዓለም የፌስቱላ ቀን በአማራ ክልል ለ4ተኛ ጊዜ በባህር ዳር ከተማ ተከብሯል፡፡

 

ማራኪ ሰውነት

ተጻፈ በመሰረት አስማረ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3158970
  • Unique Visitors: 186665
  • Published Nodes: 2579
  • Since: 03/23/2016 - 08:03