የግል መገልገያ እቃዎች ከቀረጥና ታክስ ነጻ ሆነው እንዲገቡ ተወስኗል

ባህር ዳር፡ ሰኔ 12 /2009 ዓ/ም (አብመድ)

ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸው ከሳዑዲ አረቢያ ለሚመለሱ ኢትዮጵያውያን የግል መገልገያ እቃዎች ከቀረጥና ታክስ ነጻ ሆነው እንዲገቡ ተወሰነ

ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሳውዲ የሚኖሩ ዜጎቻችን ዝቅተኛ ገቢ የሚያገኙ ስራዎች ላይ የተሰማሩ በመሆኑ በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩበት ጊዜ ባፈሩት የግል መገልገያ እቃ ላይ ቀረጥና ታክስ ለመክፈል የሚያስችል አቅም የሌላቸው መሆኑ ግልጽ ነው፡፡

በመሆኑም መንግስት እነዚህ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች ይኖሩበት ከነበረው ሳውዲ አረቢያ ተገደው ሲወጡ ይዘዋቸው የሚመጡ አነስተኛ ዋጋ ያላቸው የግል መገልገያ እቃዎች ከቀረጥና ታክስ ነጻ ሆነው እንዲገቡ በማድረግ ተገቢውን እገዛ ማድረግ እንደሚገባው ታምኖበታል፡፡

ስለዚህ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳውዲ አረቢያ በህገ-ወጥ መንገድ ይኖሩ የነበረ በመሆኑ ምክንያት ተመልሰው የመጡ መሆኑን በማረጋገጥ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት የግል መገልገያ እቃዎች ከማናቸውም ቀረጥና ታክስ ነጻ ሆነው ወደ አገር እንዲያስገቡ መፈቀዱን የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ድረ ገፅ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 1440463
  • Unique Visitors: 92861
  • Published Nodes: 1596
  • Since: 03/23/2016 - 08:03