የዜጐች ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየቀነሱ መጥተዋል፡- የአማራ ክልል ፍትህ ባለሙያዎች ማሰልጠኛ እና የህግ ምርምር ኢንስቲቲዮት

ባህር ዳር፡ ግንቦት 19/2009 ዓ/ም(አብመድ)የዜጐች ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየቀነሱ መምጣታቸውን የአማራ ክልል ፍትህ ባለሙያዎች ማሰልጠኛ እና የህግ ምርምር ኢንስቲቲዮት አስታወቀ፡፡

ኢንስቲቲዮቱ በምስረቅ አማራ ለሚገኙ 372 ዳኞች፤አቃብያን ህግ እና ለወንጀል መከላከል ፖሊሶች በወንጀለኛ መቅጫ ስርዓት፤ በወንጀል መከላከል እና በዜጐች ሰብዓዊ መብት ማስከበር ጋር በተያያዙ ህጐች ላይ ያተኮረ ስልጠና በደሴ ከተማ  ሰጥቷል፡፡

          በኢንስቲቲዮቱ የስልጠናና የህግ ምክር አገልግሎት የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ክንዳለም ይርጋ ስልጠናው በወንጀል መከላከልና በዜጐች ሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚታዩ ጥቃቅን ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲያስችል የፍትህ እና የፀጥታ አካላትን አቅም ለመገንባት ታስቦ የተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡

          የስልጠና ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የዜጐችን ሰብዓዊ መብት በማስከበር በኩል በስራ ሂደታቸው ያጋጠማቸውን ችግሮች እንዴት እንደሚፈቱ ግንዛቤ የያዙበት ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል፡፡

     ዘገባው የደቡብ ወሎ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3537599
  • Unique Visitors: 199679
  • Published Nodes: 2652
  • Since: 03/23/2016 - 08:03