የክልሉ ማዕድን ኤጀንሲ በስልጠና ሰበብ ቢሮውን ለ13 ቀን ዘግቷል-ተገልጋዮች ቢሮ መዘጋት የለበትም-የክልሉ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ

ባህር ዳር፡ ግንቦት 13/2009 ዓ/ም(አብመድ)የአማራ ክልል የማዕድን ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ በስልጠና ሰበብ ተገቢውን አገልግሎት እየሰጠ አለመሆኑን የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት በቦታው ተገኝቶ ተመልክቷል፡፡

የኤጀንሲው ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሰኢድ አሊ ለ13 ቀን አገልግሎት እንደማይኖር ማስታወቂያ ይለጠፍ እንጂ ያን ያህል ቀን ስራ አላቆምንም ፣ እሁድና ቅዳሜን ጨምሮ ስለሆነ ነው እንጂ 9 ቀን ብቻ ነው ማስታወቂያው የሚገልጠው ብለዋል፡፡ ያለንም የሰው ሀይል አነስተኛ በመሆኑ እስከ ግንቦት 20/2009 ዓ/ም  ተገልጋይ ባይመጣ ይመከራልም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ይህን የምናደርገውም በእንጅባራና በወልድያ ከተሞች የማዕድን ሀብት ልማት አደረጃጀት የሰው ሀይል ልማትን አስመልክቶ ስልጠና እየሰጠ በመሆኑ ነው፡፡

          በስልጠና ምክንያት መሉ በሙሉ አገልግሎትን ማቋረጥ እንደማይቻል የክልሉ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ገለታ ስዩም አሳስቧል፡፡ ሌሎች ሰራተኞችን በመተው አገልግሎት ክፍት መሆን አለበት፡፡ስልጠናውን እየሰጡ ቢሮን ዝግ ማድረግ አይቻልም፤ከተሀድሶ በኋላም አንዱ ሊፈታ የታሰበው እንደዚህ አይነት ችግረ ነው፡፡ስለሆነም ሀላፊዎች ለተገልጋዮች ተደራሽ መሆን አለባቸው ብለዋል፡፡

አወቀ ካሴ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3884846
  • Unique Visitors: 215544
  • Published Nodes: 2870
  • Since: 03/23/2016 - 08:03