የእንግሊዝ ዲዛይን ተቋም በጸሃይ ሃይል የሚሰራ ዋጋው ርካሽ አምፑል ሊፈጥር ነው

ባህር ዳር፡ ግንቦት 15/2009 ዓ/ም(አብመድ)የእንግሊዙ ዲዛይን አማካሪ ተቋም ከቻይና አምራች ድርጅት ጋር በመተባበር ማንም በዝቅተኛ ዋጋ ሊገዛ የሚችለውን በጸሃይ ሃይል የሚሰራ አምፑል በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ ቢቢሲ ዘገበ ፡፡

 

መቀመጫውን ማንቸስተር ያደረገው ኢንቨንቲድ የተባለው ተቋም ከቻይናው ዪንግሊ እና ቻሪቲ ሶላር ኤይድጋር በመተባበር SM100 በሚል የንግድ ስያሜ ሶላር አምፑል በማምረት በቅርቡ በ5 ዶላር ዋጋ ወደአፍሪካ ሃገራት ገበያዎች ለማውጣት አቅዷል ፡፡ በእጅ ሊያዝና በጭንቅላት ላይ ሊታሰር በሚችል መልኩ የሚሰራው አምፑል አንዴ ቻርጅ ከተደረገ ለ8 ሰዓት ያለማቋረጥ አገልግሎት ሊሰጥ እንደሚችል ተጠቅሷል ፡፡

 

አምፑሉ በ3 የአፍሪካ ሃገራት ማለትም በማላዊ ፣ኡጋንዳ እና ዛምቢያ ውስጥ በሚገኙ 9 ሺ ቤተሰቦች ተሞክሮ ውጤታማ በመሆኑ በቅርቡ ለሽያጭ እንደሚቀርብ ተነግሯል ፡፡

የኤሌክትሪክ ሃይል ለማያገኙ 6 መቶ ሚሊዮን አፍሪካውያን ብቸኛ የብርሃን ምንጫቸው በናፍጣ የሚሰራ ፋኖስ ሲሆን ዋጋው ለአብዛኛው አፍሪካዊ ውድ ከመሆኑ በተጨማሪ ለተደጋጋሚ የእሳት አደጋዎች የሚያጋልጥ በመሆኑ አዲሱ ፈጠራ ተመራጭ እንደሚሆን ይጠበቃል ፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3161878
  • Unique Visitors: 186711
  • Published Nodes: 2579
  • Since: 03/23/2016 - 08:03