የኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ መሪዎች በሻርም አል ሼክ ተወያዩ

የኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ መሪዎች በሻርም አል ሼክ ተወያዩ

 

ባሕር ዳር ፡የካቲት 15/2008 ዓ/ም(አብመድ) የኢትዮጵያ፣ሱዳን እና ግብፅ መሪዎች በግብፅ ሻርም ኤል ሼክ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

መሪዎቹ ዛሬ ግብፅ ሻርም ኤል ሼክ በተከፈተው የአፍሪካ 2016 ዓለምአቀፍ ቢዝነስ ፎረም ጎን ለጎን ነው ምክክራቸውን ያደረጉት።

 

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃሀይለማርያም ደሳለኝ ከሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር እና ከግብፁ ፕሬዚዳንት አብድልፈታህ አል ሲሲ ጋር በሶስትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተነጋግረዋል።

መሪዎቹ የሶስቱን ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ትብብር እና ግንኙነትን ማጠናከር በሚቻልበት ዙሪያም መክረዋል።

መሪዎቹ በግብፅ እንዲመክሩ የተደረገው የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም እና የግብፁ አቻቸው ሳሚህ ሹክሪ በጀርመን ሙኒክ ከተካሄደው አለም አቀፍ የፀጥታ ጉባኤ ጎን ለጎን ከመከሩ በኋላ ከስምምነት በደረሱት መሰረት ነው።

 

የግብፅ የመስኖ ሚኒስትር ሀሳም ሞጋዚ በትናንትናው እለት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ የሚካሄደውን ጥናት ከሚያካሂዱት የፈረንሳዮቹ በቢ አር ኤል እና በዴልታሬዝ ጋር ስምምነት የሚደረግበት ረቂቅ ሰነድ ላይ የሀገሪቱ መክር ቤት ተወያይቶ ማጽደቁን አስታውቀዋል።

 

ሚኒስትሩ ግብፅ ስምምነቱን ለመፈረም ዝግጁ እንደሆነች ለኢትዮጵያ እና ለሱዳን አስታውቀናል ያሉ ሲሆን፥ ስምምነቱም የያዝነው የፈረንጆቹ ወር ከመጠናቀቁ በፊት ለመፈራረም እንሰራለን ብለዋል።

 

ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን ባለፈው አመት ሰኔ ወር ላይ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር የሚረዳ የጋራ ከፍተኛ ምክር ቤት ለማቋቋም በሻርም ኤል ሼክ ከስምምነት መድረሳቸው የሚታወስ ነው።

ሰምምነቱን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣ የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ ኤል ሲሲ እና የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ተፈራርመዋል።

የምክር ቤቱ መቋቋም ሀገራቱ በተለይም በፖለቲካያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ይበልጥ ተቀራርበው እንዲሰሩ እንደሚያስችላቸው ታምኖበታል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ--http://english.ahram.org.eg/

በአማራ ቴሌቪዥን ፣በአማራ ራዲዮ እና በኤፍኤም ባህር ዳር 96.9 ዜናዎች እና ዝግጅቶች ዙሪያ ለሚኖርዎት ጥቆማና አስተያየት ለአማራ ቴሌቪዥን(ATVን)፣ ለአማራ ራዲዮ(ARን) እና ለኤፍኤም ባህር ዳር 96.9 (FMን) በማስቀደም በ8200 ማድረስ ይችላሉ::

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3161816
  • Unique Visitors: 186711
  • Published Nodes: 2579
  • Since: 03/23/2016 - 08:03