የኢራኑ ፕሬዝዳንት ሃሳን ሩሃኒ ለ2ኛ ጊዜ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫውን አሸነፉ

Newly re-elected Iranian President Hassan Rouhani gestures after delivering a televised speech in the capital Tehranባህር ዳር፡ ግንቦት 13/2009 ዓ/ም(አብመድ)የ68 አመቱ ፕሬዝዳንት ሃሳን ሩሃኒ 57 በመቶ የመራጮችን ይሁንታ በማምጣት ነው ምርጫውን ለሁለተኛ ጊዜ ያሸነፉት፡፡ ተፎካከሪያቸው ኢብራሂም ራሲ 38.5 በመቶ ድምጽ አግኝተዋል፡፡ በኢራን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ 40 ሚሊዮን መራጭ ተሳትፏል፡፡


ኢራን ከነበረችበት ብቸኝነት አውጥተው ከመላው ዓለም ጋር እንደቀላቀሏት የሚነገርላቸው ሩሃኒ ፡አክራሪነት እና ጥላቻ እንዲሁም ከዓለም መገለለን አስተሳሰብ ተፎካከሪዎቻቸው እንዲያስወግዱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡


ከአሜሪካ ጋር ያላቸው ግንኙነት ለዘብተኛ ነው እየተባሉ በአክራሪ ዜጎቻቸው የሚወቀሱት ሩሃኑ ተራማጅነት እንጂ ራስን ከዓለም ነባራዊ ሁኔታ አግልሎ መኖር ማንንም አይጠቅምም ፡፡ በመሆኑም እያንዳንዱ ኢራናዊ ለሀገሩ እድገት ሲባል ድጋፍ ሊያደርግልኝ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ከመራጩ 40 ሚሊዮን ድምጽ የ23 ሚሊዮኑን ድጋፍ ያገኙት ፕሬዝዳንት ሃሳን ሩሃኒ ስትተቹኝና ስትቃወሙኝ የነበራችሁ ኢራናውያንን በሙሉ ሀሳባቸሁን አከብራለሁ፡፡ከአሁን በኋላ ደግሞ ለሀገራችን እድገት አብረን እንጓዛለን ብለዋል፡፡


ኢራን ከ79 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሚኖርባት ሀገር ስትሆን በቀጣይ ለፕሬዝዳንት ሃሳን ሩሃኒ ፈተና ይሆናል የተባለውም 10 በመቶ የደረሰው ስራ አጥነት ነው፡፡
ቢቢሲና ኤኤፍፒ እንደዘገቡት ሀሳን ሩሃኒ ኢራንን ከመሯት መሪዎች የሚለያቸው የተራማጅ ሀሳብ አቀንቃኝ እና ኢራን ከዓለም መገለል የለባትም ብለው የሚያምኑ መሪ መሆናቸው ነው፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3537594
  • Unique Visitors: 199679
  • Published Nodes: 2652
  • Since: 03/23/2016 - 08:03