የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሐሰት ምስክርነት እና የውሳኔ መጓተት ችግሮችን መቅረፍ አልቻለም-ተገልጋዮች

ባህር ዳር፡ ግንቦት 14/2009 ዓ/ም(አብመድ)በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተካሄደው የጥልቅ ተሃድሶ እንቅስቃሴ በፍርድ ሂደት ላይ የሚታዩ የሐሰት ምስክርነት እና የውሳኔ መጓተት ችግሮችን መቅረፍ እንዳልቻለ ተገልጋዬች ተናገሩ፡፡

አገልግሎት ለማግኘት በግቢው ያገኘናቸው ወይዘሮ ደብሬ ወርቁ ‹‹የውሸት ምስክር ነው ሀገሩን ህልም ያደረገው፡፡ስራ ሲያጡ ተደራጅው እየሰሱ በሀሰት እያንገላቱን ነው ብለዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ ከጥልቅ ተሀድሶ ማግስት ያሉበትን ችግሮች ለመቅረፍ ቢሞክርም በህብረተሰቡ ላይ እርካታን መፍጠር አልቻለም፡፡

 

የፍርድቤቱ ፕሬዝዳንት አስፋው  አረጋ የሀሰት ምስክርነት በፍርድቤቱ ብቻ በተናጠል የሚመጣ አይደለም ፡፡የሌሎች ቅንጅታዊ አሰራርን እንደሚጠይቅ በመናገር፡፡አቃቢ ህግ በንቃተ ህግ ሀሰተኛ ምስክርነትን ማስገንዘብ አለበት ፣ፖሊስ ደግሞ ንቃተ ህግ መስጠት አለበት ሲያጣራም እንዲሁ ብለዋል፡፡

የፍርድቤቱ ፕሬዝዳንት አስፋው  አረጋ  እንዳሉት የውሳኔ መጓተት ግን የፍርድቤቱ መገለጫ አይደለም ነው ያሉት፡፡ከመረጃ አቀራረብ ጉድለት የሚከሰት ነው የሚሆነውም ብለዋል፡፡

አልፎ አልፎ ካልሆነ በ30 ቀን ውስጥ ነው መዝገብ የሚወሰነው፡፡ከዚህ ውስጥ አንድ ሰው እንኳ ቢጓተት ችግሩ የማስረጃ አቀራረብ ነው ሊሆን የሚችለው፡፡በወንጀል ነው ወይስ በፍትሃ ብሄር የሚለው ካለመለየትም ይከሰታል ብለዋል፡፡

 

 

 

     

ቴዎድሮስ ወርቁ

ተጻፈ በመሠረት አስማረ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3527376
  • Unique Visitors: 199329
  • Published Nodes: 2627
  • Since: 03/23/2016 - 08:03