የንጉስ ላሊበላ እረፍት ፤ ዛሬ ነበር ሰኔ 12

ባህር ዳር፡ ሰኔ 12 /2009 ዓ/ም (አብመድ)ዮዲት ጉዲት የአክሱምን ስልጣኔ ስታመክነው የኢትዮጵያ ስልጣኔ እንደገና በሮሃ መንደር በላሊበላ እንደገና ተወለደ፡፡የዛግዌ ስርዎ መንግስት ከ 922-1263 ዓ/ም አካባቢ ድረስ ዘልቋል፡፡ ከ1263 (71)ዓ/ም በኋላ በአቡነ ተክለሃይማኖት ተማሪ በንጉስ ይኮኖአምላክ አማካኝነት የዛጉዌ ስርዎ መንግስት ቀዝቅዞ የሰለሞናዊ ስርዎ መንግስት ተነስቷል፡፡በሁለቱ ስርዎ መንግስታት መካከል የጎላ ልዮነት

ከዛጉዌ ከተነሱ ነገስታት መካከል ንጉስ ላሊበላ ደማቁን ታሪክ ይይዛል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት ዕለት ታህሳስ 29 ቀን በ 1101 ዓ/ም ንጉስ ላሊበላ ካህንም ነበሩ፡፡በክህነታቸው የቅድስና ማዕረግ ተችሯቸዋል፡፡ በጎጃም በጎንደር ፣ በሸዋ ተመላልሰው የቤተክርስቲያን ትምህርት ተምረዋል፡፡ በእየሩሳሌምም ለ 12 ዓመት ቆይተው እብራይስጥ እና አረበኛ ቋንቋዎችን ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ በ1157 ዓ/ም ወደ ስልጣን ሲመጡ እየሩሳሌምን በሮሃ አስመስለው ገነቡ፡፡

የላሊበላ ህንፃዎች በዓለም በዮኔስኮ ከተመዘገቡ 1051 የታሪክ ሀብቶች መካከል ላሊበላ ከስምንቱ አስደናቂ የዓለም ቅርሶች መካከል አንዱ ነው፡፡ 
ከአባታቸው ዣንስዮም እና ከእናታቸው ኬዮርና የተወለዱት ለ 40 ዓመታት በስልጣን ሲቆዮ የራሳቸው መኖሪያ ቤት አልነበራቸውም፡፡ በድንኳን እየኖሩ የላሊበላ ህንፃዎችን አነፁ፡፡ ንጉስ ላሊበላ፣ ከግብፅ ጋር የሀይማኖት ክርክር ቢነሳባቸው አባይን ለመገደብ ሙከራ አድርገዋል፡፡ የአባይ የመገደብ ሙከራ ከላሊበላ እስከ ቀዳማዊ ሀይለስላሴ ድረስ ነበረ፡፡ነገር ግን በዲፕሎማሲዊ ግንኙነት ምክንያት ሙከራው ሳይተገበር ቀረ፡፡


ፕሮፊሰር ሪቻርድ ፓንክረስት፣የንጉስ ላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት በዓለም ላይ ፍፁም ልዮዎች ናቸው፡፡ይሄም አብያተክርስቲያናቱ ፣ በሀገር ውስጥ ሰዎች ብቻ እንደተሰሩ ማሳያ ነው፡፡ ንጉስ ላሊበላ በተወለዱ በ 97 ዓመታቸው ሰኔ 12 ቀን አርፈዋል፡፡

በየሺሃሳብ አበራ
ለህብረተሰብ ለዉጥ እንተጋለን!!
የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት
አማራ ቴሌቪዥን ፣በአማራ ራዲዮ እና በኤፍኤም ባህር ዳር 96.9 ዜናዎች እና ዝግጅቶች ዙሪያ ለሚኖርዎት ጥቆማና አስተያየት ለአማራ ቴሌቪዥን(ATV)፣ ለአማራ ራዲዮ(AR)፣ ለኤፍኤም ባህር ዳር 96.9 (FM)ለደብረ ብርሃን ኤፍኤም 91.4 (DBFM) ፣ለደሴ ኤፍኤም 87.9(DFM) እና ለበኩር (AB) በማስቀደም በ8200 ማድረስ ይችላሉ::

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3870233
  • Unique Visitors: 214838
  • Published Nodes: 2859
  • Since: 03/23/2016 - 08:03