የቱኒዚያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስናን ለመዋጋት የጸረ-ሙስና አዋጅ አወጁ፡-ህዝቡም በሰልፍ ድጋፉን እየለጸ ነው

ባህር ዳር፡ ግንቦት 19/2009 ዓ/ም(አብመድ)በቱኒዝያ እየተንሰራፋ ያለው ሙስና ህዝቡን  እጅግ እየጎዳ ነው የሚሉት የቱኑዝያ ህዝቦች  በዋና ከተማዋ ቱኒዝ ውስጥ ሙስና ለመዋጋት ጠቅላይ ሚኒስትር ዮሴፍ ቻሃድ በሚያደርጉት መጠነሰፊ እንቅስቃሴ  ማህበረሰቡ ድጋፍ ለመስጠት ሲል የድጋፍ ሰልፍ አካሂዷዋል፡፡

የቱኒዚያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዮሴፍ ቻሃድ በመላው አገሪቱ የፀረ-ሙስና  ትግል  አውጀዋል፡፡

አዋጁ ከታወጀ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ በህብረተሰቡ ጥቆማ በሙስና የተጠረጠሩ በርካታ የቱኒዚያ  ነጋዴዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ ማህበረሰቡን እጅግ ያማረረውን ሙስና ለመታገል መንግስት እርምጃ በወሰደ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ቱኒዝያ ውስጥ የሚኖረው ማህበረሰብ ሙስናን ያስፋፉ ሰዎችን አጋልጦ በመስጠት እየተባበረ ነው ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙስናን ለመዋጋት የአንድ ወቅት ዘመቻ ብቻ ሳይሆን ከህብረተሰቡ ጋራ በጋራ እስከመጨረሻው ድረስ የምንታገለው ነው፡፡ ለዚህም ማህበረሰቡ አሁን ያሳየውን ተነሳሻነት ወደፊትም አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡

ምንጭ፡-አፍሪካ ኒውስ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3161865
  • Unique Visitors: 186711
  • Published Nodes: 2579
  • Since: 03/23/2016 - 08:03