የተሻሻለው የገቢ ግብር ረቂቅ አዋጅ ይፋ ሆነ

የተሻሻለው የገቢ ግብር ረቂቅ አዋጅ ይፋ ሆነ

 
የተሻሻለው የገቢ ግብር ረቂቅ አዋጅ ይፋ ሆነ
 

ባሕር ዳር፡ግንቦት 29/2008 ዓ/ም(አብመድ) የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የተሻሻለውን የገቢ ግብር ረቂቅ አዋጅ ይፋ አደረገ።

የሚኒስቴሩ የህግ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ዋሲሁን አባተ፥ ረቂቅ አዋጁ ከዚህ በፊት ከነበረው የተሻሻለ መሆኑን ተናግረዋል።

ረቂቅ አዋጁ ተቀጣሪ ሰራተኞች አሁን እየከፈሉት ያለውን የገቢ ግብር መጠን እንዲቀንስ የሚያደርግና፥ የህብረተሰቡን ገቢ ከግምት ያስገባ የገቢ ግብር ምጣኔ፣ ዝቅተኛ እና ከፍተኛ ተብሎ የተቀመጠውን የደመዎዝ የግብር ጣሪያን የሚያሻሽልም ነው።

በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ መሰረት ደመዎዛቸው ከ6 መቶ ብር በታች የሆነ ተቀጣሪ ሰራተኞች ግብር አይከፍሉም።

በመጭው ሃሙስ እና ዓርብም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከንግዱ ማህበረሰብ፣ ከውጭ ሃገር ኩባንያዎች እና ከሙያ ማህበራት ጋር ውይይት ይደረግበታልም ነው ያሉት አቶ ዋሲሁን።

በውይይት ዳብሮ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ከቀረበ በኋላም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2008 ዓ.ም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ፥ ከሃምሌ 1 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ ፀድቆ ስራ ላይ እንዲውል እየተሰራ መሆኑንም ነው የተናገሩት። 

 

በዚህም መሰረት ከመቀጠር በሚገኝ ገቢ ላይ ለሚጣለው ግብር ተፈጻሚ የሚሆኑትን ምጣኔዎች በሚከተለው መልኩ አስቀምጧል፤

income_tax_1.png

 

ሚኒስቴሩ ከዚህ ባለፈም በመኖሪያ ቤት እና በድርጅት ኪራይ የሚገኝ ገቢ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ ምጣኔዎችንም ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት በኪራይ በሚገኝ ገቢ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑት ምጣኔዎችን በሚከተለው መልኩ አስቀምጧል፤

 

income_tax_2.png

 

ምንጭ፡-ኤፍቢሲ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3872472
  • Unique Visitors: 214892
  • Published Nodes: 2859
  • Since: 03/23/2016 - 08:03