የስራ ምዘና እና የደረጃ አወሳሰን በ2009 ዓ.ም በሁሉም ተቋማት ይተገበራል

ባሕር ዳር፡ሚያዝያ 18/2008 ዓ/ም(አብመድ)የመንግስት ሰራተኞች የስራ ምዘና እና የደረጃ አወሳሰን ፕሮጀክት በ2009 ዓ.ም በሁሉም ተቋማት ይጀመራል ብለዋል በምክትል ጠቅላይ ሚንስተር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ሪፎርም ክላስተር አስተባባሪና የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ሚንስትራ አስቴር ማሞ።

ፕሮጀክቱ በዚህ አመት ሚያዝያ ወር ላይ በተመረጡ ተቋማት የሙከራ ስራ ይጀምራል ቢባልም እስካሁን ተግባራዊ እየተደረገ አይደለም

ሚኒስትሯ ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ9 ወራት ሪፖርት  አቅርበዋል።

በእስካሁኑ ሂደት የምዘና መስፈርቶችን የማጥራት ተግባራት በስፋት የተከናወኑ ሲሆን፥ አማራጭ የደረጃ አወሳሰን ስልቶችም ተቀይሰዋል።የስራ ምዘና እና የደረጃ አወሳሰን በ2009 ዓ.ም በሁሉም ተቋማት ይተገበራል

ምዘናው የአገልጋይነት ባህሪን በመለካት የተሻለ የመንግስት ሰራተኛን ለመፍጠር አልሞ የተዘጋጀ እና ከክህሎት ባሻገር የስነ ባህሪ እና የአገልጋይነት ስነ ልቦና የሚለካ መሆኑም ነው የተነገረው።

በአሁኑ ወቅት በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን "ከሚያዚያ 2008 ዓ.ም ጀምሮ በመንግስት ተቋማት የደመወዝ ማስተካከያ ይደረጋል" በሚል እየተናፈሰ የሚገኘው መረጃም ትክክለኝነት የሚጎለው መሆኑን ነው ሚኒስትሯ ያብራሩት።

ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ከ1964 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ በስራ ላይ ያለው የስራ ምደባ ዘዴ በሲቪል ሰርቪሱ ካለው የስራዎች ብዛት፣ ውስብስብነትና ባህሪ እንዲሁም ከትምህርት ስርዓቱ ጋር አብሮ የማይሄድ ነው።

በመሆኑም ይህን ከመሰረቱ መቀየር የሚችል ስራዎችን የመመዘንና ለእኩል እኩል ክፍያን መፈፀም የሚያስችል ስልትን መተግበር ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

ፕሮጀክቱ በተመረጡ ተቋማት ከሚያዚያ ጀምር እንደሚተገበር በመገለፁ ለምን እስካሁን ለምን አልተተገበረም ለሚለው ሚኒስትሯ ምላሽ ሰጥተውበታል።

ከእንዚህ መካከል አንዳንድ ተቋማት የስራ ዝርዝር እንዲያቀርቡ በተሰጣቸው ጊዜ አለማቅረባቸው፣ በሌሎች ተቋማት ውስጥም መረጃዎች ተሟልተው አለማቅረባቸው ተጠቅሰዋል።

በመሆኑም መረጃዎችን የማጥራት ስራው ከተጠናቀቀ በኋላ የስራ ምዘና እና የደረጃ አወሳሰን ፕሮጀክት በ2009 ዓ.ም በሁሉም ተቋማት እንደሚተገበር ነው የገለፁት።

መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ አኳያ ሥር ነቀል ለውጥ ለማምጣትና ለህዝቡ ቅሬታ ትክክለኛና ብቃት ያለው ምላሽ ለመስጠት አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ከህብረተሰቡ፣ ከተቋማት እና አመራሮች ጋር በየጊዜው የሚደረገው ውይይት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ወይዘሮ አስቴር ያስታወሱት።

 

ኤፍ.ቢ.ሲ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3527412
  • Unique Visitors: 199331
  • Published Nodes: 2627
  • Since: 03/23/2016 - 08:03