የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የአርብቶ አደሩን ኑሮ በሚለውጡ የምርመር ስራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው-ከአማራ ቴሌቪዥን ጋር አመራሮች ቆይታ አድርገዋል

ባህር ዳር፡ ግንቦት 15/2009 ዓ/ም(አብመድ)ከተመሰረተ 9 አመታትን ያስቆጠረው ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በ7 ኮሌጆች ፣በ38 የትምህርት ክፍሎች ከ8ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ዘላቂነት ያለው ልማትለአርብቶ አደሩና ለከፊል አርብቶ አደሩ በሚል መሪ ሀሳብ የጥናትና ምርምር ጉባኤ አካሂዷል፡፡በቀረበው ጥናት መሰረትም አርብቶ አደሩ ከሌሎች ጋር ሲነጻጸር በኑሮው ላይ ለውጥ አላመጣም የሚል ይገኝበታል፡፡

ጥናቱን ያቀረቡት አቶ አቡበክር ሙመድ እንዳሉት አፋር አካባቢ መስኖ ውሃ አለ፡፡በአግባቡ እየተጠቀምናቸው አይደለም፡፡ለመስኖ የተመቸውንም መሬት በአግባቡ እየተጠቀምነበት አይደለም፡፡የአርብቶ አደሩን ህይወት በሚቀይርም በኩል መሰራት አለበት ብለዋል፡፡

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ መሀመድ አህመድ እነደገለጹት ምርምሮች የማህበረሰቡን ችግር እንዲፈቱ በቂ ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡የተሻለ ተመራማሪ እንዲፈጠርም ማበረታቻ በማድረግ ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠርን ነው ብለዋል፡፡

አርብቶ አደሩ በቂ ውሃ እና የእንስሳት መኖ በሌለበት አካባቢ ያሉ ሰዎች በአንድ ላይ ሰብሰብ ብለው እንዲኖሩ ዩኒቨርሲቲው እየሰራ ነው ያሉት የሰመራ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝደንት አቶ አሊ ሁሴን ናቸው፡፡ምርምሮች ለህብረተሰቡ ለውጥ የሚያመጡ እንዲሆኑ ከመደርደሪያ ተንጠልጥለው ሳይሆን መሬት ወርደው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር እንዲፈቱ በትክክል እንዲቃኙ ጥረቶች አሉ ከጊዜ ወደ ጊዜም ተሻሽሏል ብለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው 4ተኛውን ሃገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ጉባኤ ከግንቦት 12 እስከ 13 በሰመራ ከተማ አካሂዷል፡፡

ሰለሞን አወቀ

ተጻፈ በመሰረት አስማረ

 

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3537595
  • Unique Visitors: 199679
  • Published Nodes: 2652
  • Since: 03/23/2016 - 08:03