የሞሮኮ መመለስ ለአፍሪካ ህብረት ተጨማሪ አቅም ነው -የፓን አፍሪካ ፓርላማ ፕሬዝዳንት

 

Image may contain: 1 person, sittingጥር 22 / 2009 ዓ.ም (አብመድ) የፓን- አፍሪካን ፓርላማ ፕሬዝዳንት የሆኑት ሮጀር ንኮዶ ዳንግ እንደገለፁት ሞሮኮ ድጋሚ ወደ ህብረቱ መቀላቀሏን ይደግፋሉ፡፡

ሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ወደ ህብረቱ የመመለሷ እርምጃ ለአህጉራዊ ድርጅት ዋጋ ይጨምራል ነው ያሉት፡፡

“ሞሮኮ አፍሪካዊት ሀገር ነች በመሆኑም በጋራ ጉዳዮቻችን ዙሪያ አንድ ላይ እንድንመክር ያስችለናል ‘’ብለዋል፡፡

እየተካሄደ በሚገኘው 28ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ይህን አስተያየት የሰጡት ፕሬዝዳንት ሮጀር ንኮዶ፤ ሞሮኮ መመለሷ ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ ለማምጣት የሚደረገው ጥረት እንዲጠናከር ያደርጋል፡፡

ሞሮኮ ከሶስት አስርት አመታት በኋላ ወደ ኅብረቱ ለመመለስ ጥያቄ ያቀረበች ሲሆን ጥያቄዋም በመሪዎቹ ስብሰባ ምላሽ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ለመመለስ በወሰደችው እርምጃ አድናቆት እና ድጋፋቸውን ለግሰዋል፡፡

የህብረቱ መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ የሚካሄደው 28ኛው ጉባዔ እስከ ነገ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

 

ምንጭ፡ኢዜአ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3527462
  • Unique Visitors: 199331
  • Published Nodes: 2627
  • Since: 03/23/2016 - 08:03