የማዕከላዊ አፍሪካ ሃገራት የትምህርት ቤት ፆታ ልዩነትን እያጠበቡ ነው፡፡

ባህር ዳር፡ ግንቦት 14/2009 ዓ/ም(አብመድ)በሰሜን እና ደቡብ አፍሪካ ሃገራት ውስጥ ከወንዶች ይልቅ ወጣት ሴቶች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ሳያስተጓጉሉ እንደሚያ ጠናቅቁ የአፍሪካ ልማት ባንክ ጥናት ማመላከቱን ቢቢሲ ዘግቧል ፡፡

በማእከላዊ አፍሪካ ክልል በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚታየው የጾታ ልዩነት እየጠበበ መምጣቱን የተሠራው ጥናት ቢያሳይም በአህጉር ደረጃ ግን ትምህርታቸውን የሚያጠናቅቁ ሴቶች ቁጥር አናሳ እንደሆነ ታውቋል ፡፡

በትምህርት ቤቶች ያለውን የጾታ ልዩነት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጥበብ የተከናወነው ስራ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ ሲሆን አሁን በተገኘው መረጃ መሠረት እ.ኤ.አ. በ2005 ከነበረው አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የሚያጠናቅቁ ሴቶች አሃዝ በሶስት እጥፍ ማደጉ ታውቋል፡፡ እንደ አለም ባንክ ሪፖርት ከሆነ የአፍሪካውያን ሕይወት ቀጣይነት ባለው መልኩ መሻሻል እየታየበት ነው፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3537566
  • Unique Visitors: 199679
  • Published Nodes: 2652
  • Since: 03/23/2016 - 08:03