የሃይማኖት እና የጎሳ መሪዎች ተፈጥሮን ለመጠበቅ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ እየመከሩ ነው

ባህር ዳር፡ ሰኔ 12 /2009 ዓ/ም (አብመድ)

የሃይማኖት እና የጎሳ መሪዎች ዛሬ በጀመሩት የውይይት መድረክ ላይ የትሮፒካል ደን አካባቢ ተፈጥሮን ለመጠበቅ የተለያዩ ስልቶች ሊነደፉ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ኖርዌይ ባዘጋጀችው በዚህ መድረክ ላይ መሪዎቹ እንዳሉት ዓለም አቀፋዊ የአየር ንብረት ለውጥ ውሳኔዎች ማዘግየትም ሆነ ላለመፈጸም መወሰኑ በትውልድ ላይ እንደመፍረድ ይቆጠራል ብለውታል፡፡

የክርስቲያን ፣ሙስሊም፣ የአይሁድ፣ የሂንዱ ፣ቡዲስት እና የዳዎይስት ተወካዮች ኦስሎ ውስጥ ከጎሳ መሪዎች ጋር ተገናኝተው ሲመክሩ እንዳሉት ደኖችን ሊጠብቅ የሚችል ስነምግባር ያለው ማህበረሰብ መፍጠር ከሃይማኖት እና ከጎሳ መሪዎች የሚጠበቅ ሃላፊነት ነው ብለዋል፡፡

ለእርሻ ስራ ሲባል የሚመነጠረውን የተፈጥሮ ሃብት በመጠበቅ በአለም ላይ የተደቀነውን የበረሃማነት ስጋት መቀነስ ይገባል ብለዋል መሪዎቹ፡፡

የኖርዌይ የአየር ንብረት እና የአካባቢ ሚኒስትር ቪዳር ኤልግሰን ከ ሰኔ 19-21 እየተከናወነ ባለው የውይይት መድረክ ላይ በመገኘት ለመሪዎቹ ባስተረላለፉት መልእክት እንዳሉት ደኖች በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች የገቢ ምንጭ ናቸው፡፡

በመሆኑም ከሚደርስባቸው ጉዳት ለመጠበቅ የሃይማኖት መሪዎቹ ትልቅ ሚና አላቸው፡፡ በማህበረሰቡም ተሰሚነታቸው ትልቅ በመሆኑ ልታስተምሩ ይገባል ብለዋል፡፡
ለዘንባባ ዘይት ማምረት የሚሰጠው ፍቃድ እና ልቅ የከብቶች ግጦሽ ማቆም ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

በተባበሩት መንግስታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት እንደሚለው የዓለም ደን ስፋት ከ2010-2015 ባለው ጊዜ ውስጥ 33ሺ ካሬ ኪሎ ሜትር (12ሺ 7 መቶ ካሬ ኪሎ ሜትር) የደረሰ ሲሆን ይህም ስፋቱ የቤልጂየምን የቆዳ ስፋት ያክላል፡፡

መሪዎቹ በውይይታቸው እንዳሉት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ተፈጥሮን ሊጎዱ በሚችሉ ኢንቨስትመንቶች ላይ ገደብ እንዲኖር ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

ምንጭ፡-ሮይተርስ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 1440469
  • Unique Visitors: 92861
  • Published Nodes: 1596
  • Since: 03/23/2016 - 08:03