ዛንዚባር የኮሌራ ወረርሽኝን ለመከላከል የመንገድ ላይ ምግብ ሽያጭን ከለከለች፡፡

ባህር ዳር፡ ግንቦት 22 /2009 ዓ/ም(አብመድ) በዛንዚባር ከፊል ደሴቶች ላይ ከባድ ዝናብ ጥሎ የተፈጠረው ጎርፍ የንጽህና ችግር አስከትሎ ኮሌራ በመቀስቀሱ ምክንያት የመንገድ ላይ ምግቦች እንዳይሸጡ መንግስት ክልከላ ማድረጉን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡

Image may contain: people sitting, table, food and indoor
ከግንቦት መጨረሻ ጀምሮ ለእስልምና እምነት ተከታዮች የረመዳን ቅዱስ ወር በመሆኑ ሰዎች ከጾሙ በኋላ ምሽት ላይ ምግብ በጋራ መመገብ የተለመደ መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውሶ የበሽታውን ሥርጭት ለመቀነስ በየቤቱ የሚጋብዟቸውን ሰዎች ቁጥር እንዲቀንሱ አሳስቧል ፡፡
በዛንዚባር የተከሰተው ወረርሽኝ የኮሌራ በሽታ ለመሆኑ የተረጋገጠው በቅርቡ 23 አዳዲስ የበሽታው ተጠቂዎች በምርመራ ከተለዩ በኋላ ነው ፡፡ 
የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ፒምባ ጁማ እንደተናገሩት የኮሌራ ምልክቶች ሲታዩ በአፋጣኝ በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ ለነዋሪዎቹ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በ2016 በበሽታው ተይዘው ከነበሩት 4330 ሰዎች ውስጥ 68ቱ ለህልፈተ- ህይወት መዳረጋቸውን የታንዛኒያ መንግስት አስታውቋል ፡፡

ምንጭ፡-ሲ ጂ ቲ ኤን

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3537583
  • Unique Visitors: 199679
  • Published Nodes: 2652
  • Since: 03/23/2016 - 08:03