ዛሬ ስለ አለቃ ዘነብ መረጃ እንስጣችሁ

ባህር ዳር፡ ሰኔ 12 /2009 ዓ/ም (አብመድ)

አለቃ ዘነብ ኢትዮጵያዊ ታሪክ ሰርቶ ታሪክ ያላስታወሰው በዘመኑ የነበረ የጥበብ ነፍሰጡር ነው፡፡ አለቃ ዘነብ ከሸዋ ወደ ጎንደር ለትምህርት እንደመጣ ተክለፃድቅ መኩሪያ ፅፈዋል፡፡ ዘነብ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ ተጠምቆ፣በጥበብ እና በምርምር ወልፍ የተያዘ ባለምጡቅ ልዕለ አዕምሮ ነው፡፡

ፍልስፍና በዘርያቆብ ተጀመረ፡፡ዘርያቆብ ጠያቂ አዕምሮን የታደለ የዘመኑ ተራማጅ የቀለም ቀንድ ነው፡፡ብዙ ጊዜውን በጎንደር ያሳለፈው ዘርያቆብ ተማሪው ወልደ ህይወትን ልክ እንደግሪኮቹ ሶቅራጠስ፣አርስቶትል፣ፕሉቶ፡፡በዘርያቆብ እና በወልደ ህይወት ፍልስፍናን እስከ አለቃ ዘነብ የትውልድ ክፍተት ቢኖርም አለቃ ዘነብ ግን የወረሰው ይመስላል፡፡ሶስቱም ሃይማኖትን፣ባህልና እና ህይዎትን ይፈላሰፉበታል፡፡

"መፅሀፈ ስጋዊ ወ መንፈሳዊ " በአለቃ ዘነብ የተከተበ የፍልስፍናና የምርምር መፅሐፍ ነው፡፡በያኔው ዘመን፣ኢትዮጲያዊያን የባህልና የሀይማኖት እስረኛ ነበሩ፡፡ በእርግጥም፣የኢትዮጵያ ስልጣኔ የውሀ ልኩ የተገነባው ከሀይማኖት ነው፡፡ አለቃ ዘነብ ግን ሰው ለሀይማኖቱ ብቻ እስረኛ ሳይሆን ለምድራዊ ኑሮው እንዲተጋ በመፅሀፉ ቀሰቀሰ፡፡

እነሆ ለአብነት፣ " ድንጋይ ና ጭቃ ቢቀጣጠሉ ታላቅ ቤት፣ረዥም ቅጥር ይሆናል፡፡እናንተም መሬታውያን ሰዎች እንዲህ ብትረዳዱ ጥበባችሁ ከሰማይ በደረሰ" ሲል በመፅሀፉ ይገስፃል፡፡ "

አለቃ ዘነበ ውስጠ ወይራ ደራሲ ነው፡፡ በሀይማኖት ላይ ይፈላሰፋል፡፡ የእውነት እና የእሳቤ ጥጉ ሲመዘን ግን ከሀይማኖት አስተምሮ የወጣ አልነበረም፡፡ ያኔ አለቃ ዘነበ የምዕራባውያን ያደገ ጭንቅላት የእሳቤ ምንጭ ለመቅዳት የጥያቄ ማድጋውን አዘጋጀ፡፡ማድጋውንም በመሙላት የአፄ ቴወድሮስን ልጅ ልዑል አለማየሁን ያስተምረው ነበር፡፡

የጋፋቱ እንግሊዛዊ እስረኛ ዶክተር ሄኔሪ ብላክ ስለአለቃ ዘነበ ይሄን መስክሯል ፡፡ " አለቃ ዘነበ በእውቀት ፍለጋ ፣በሀበሻዊነቱ የማይደራደር የጥበብ ፍጡር ነው፡፡ ዘነበ ስለጨረቃ ፣ ስለ ስነ ህዋ ሳይንስ ይጠይቃል፡፡" ሲል ስለ አለቃ ዘነብ ኢትየጵያዊ መስክሯል፡፡

አለቃ ዘነብ መቼ እንደሞተ አይታወቅም፡፡ ብቻ ከእሱ በላይ ዘመንን የቀደመ እሳቤው ይታወቃል ፡፡ ከአለቃ ዘነብ በኋላ እንደ ሼህ ጄብሪል፣እንደ አለቃ ገብረሃና የመሰሉ ፈላስፋዎች ብቅ ብለዋል፡፡

በየሺሃሳብ አበራ

ለህብረተሰብ ለዉጥ እንተጋለን!!
የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት

አማራ ቴሌቪዥን ፣በአማራ ራዲዮ እና በኤፍኤም ባህር ዳር 96.9 ዜናዎች እና ዝግጅቶች ዙሪያ ለሚኖርዎት ጥቆማና አስተያየት ለአማራ ቴሌቪዥን(ATV)፣ ለአማራ ራዲዮ(AR)፣ ለኤፍኤም ባህር ዳር 96.9 (FM)ለደብረ ብርሃን ኤፍኤም 91.4 (DBFM) ፣ለደሴ ኤፍኤም 87.9(DFM) እና ለበኩር (AB) በማስቀደም በ8200 ማድረስ ይችላሉ::

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 1440500
  • Unique Visitors: 92862
  • Published Nodes: 1596
  • Since: 03/23/2016 - 08:03