ቡሪንዲ ያገቡ እና የወለዱ ሰዎች እንደገና ጋብቻ እንዲፈጽሙ ትዕዛዝ አስተላለፈች

ባህር ዳር፡ ግንቦት 19/2009 ዓ/ም(አብመድ)ያልተጋቡ ጥንዶች ግን ደግሞ አብረው የሚኖሩ እና የወለዱ ሰዎች ያላቸውን ግንኙነት ሕጋዊ ለማድረግ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ቀነገደብ ተቆርጦላቸዋል፡፡

እንደ ቡሩንዲ መንግስት ገለጻ ከሆነ በአገሪቱ ውስጥ የሥነ ምግባር ተሃድሶ ለማካሄድ ሃገሪቱ የምታካሂደው ጥረት አካል ነው ብሏል፡፡

ትዕዛዙ ከፕሬዚዳንት ፒየር ኒኩሪንዚዛ የተላለፈ ሲሆን ጉዳዩን የሃገሪቱ የእምነት ተቋማት ደግፈውታል ፕሬዘደንቱ ህጉን ውጤታማ ለማድረግ በዚህ ወር አንድ ዘመቻ በማድረግ እየተንቀሳቀሱ ናቸው፡፡

እንደ ፕሬዘዳንቱ ገለጻ ከሆነ ህጋዊ ያልሆኑ ሙሽሮችን ህጋዊ በማድረግ እርስ በርሳቸው ያላቸውን ፍቅር እንዲገልጹ  እና ለአገራቸው ያላቸውን ቀና አስተሳሰብ በማዳበር ብሄራዊ አንድነትን ለማምጣት ያስችላል ብለውታል፡፡

መንግስት ካለፈው አመት ጀምሮ የጋብቸ ህጋዊነት ላይ ህግ አውጥቶ በመላው አገሪቱ የወለዱ ሰዎች ጭምር እንደገና ህጋዊ ጋብቸ እንዲፈጽሙ ጫና  እያደረገ ይገኛል፡፡

ሃገሪቱ ህጋዊ ያልሆኑ ጋብቻዎችን በጋራ በተዘጋጀ የሰርግ ስነ-ስርአት ወደ ህጋዊነት እንዲመጡ እያደረገች ትገኛለች፡፡

የቡሩንዲ የሃገር ውስጥ ቃል አቀባይ ቴሬንስ ናታሂራጃ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል እንዳሉት በቡሩንዲ በህገወጥ ትዳር ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ጥቂት አይደሉም ካሉ በኋላ ከአንድ በላይ ማግባትን ጨምሮ  በትምህርት ቤት ያሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ለአላስፈላጊ እርግዝና እና ውርጃ በመጋለጥ ከትምህርታቸው እንደሚስተጓጎሉ እና ለሞት እንደሚዳረጉ ገልጸዋል፡፡

ሰዎችን ህጋዊ ጋብቸ እንዲፈጽሙ በማድረግ በመሃል ቤት የሚጎዱ የቡሩንዲ ህጻናትን መታደግ ይገባል ካሉ በኋላ በዚህ አመት ከ50ሺህ በላይ ህጻናት ያላሳዳጊ በመቅረታቸው እና በተለያየ ቦታ ተጥለው በመገኘታቸው መንግስት አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርግ ተገዷል ብለዋል፡፡

ምንጭ፡-አልጀዚራ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3537619
  • Unique Visitors: 199679
  • Published Nodes: 2652
  • Since: 03/23/2016 - 08:03