በውሃ ወለድ በሽታ 230 ሱዳናውያን ሞቱ

 

ባህር ዳር፡ ሰኔ 12 /2009 ዓ/ም (አብመድ)

በሱዳን የውሃ ሚኒስትሩ ኢድሪስ አቡ ጋርዳ እንዳሉት ከአንድ አመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ 230 ሰዎች በውሃ ወለድ በሽታ ለህልፈተ ህይወት መዳረጋቸውን አስረድተዋል፡፡

ሚኒስትሩ ኢድሪስ አቡ ጋርዳ ለአናዶሉ የዜና ወኪል እንደተናገሩት የውሃ ወለድ በሽታ ስርጭቱን መግታት ቢቻልም በህብረተሰቡ የእውቀት ማነስ አሁንም ለህልፈተ ህይወት የሚዳረገው ሰው ቁጥር ብዙ ነው ብለዋል፡፡

እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ ከሆነ አሁን ላይ በተደረገ ምርመራ 16ሺ ሰዎች በውሃ ወለድ በሽታ ተጠቅተዋል፡፡ በ2030 በሽታውን ከሱዳን ለማጥፋት እየሰራን ነው ቀስ በቀስም ቁጥሩ እየተመናመነ ነው ብለዋል፡፡

አሁን ላይ የክረምት ወቅት በመሆኑ እና በሽታው በሰፊው የሚከሰት በመሆኑ ሰፊ ስራ መስራት እና ህብረተሰቡን ማንቃት ያጠበቅብናል የሚሉት ሚኒስትሩ ውሃን አፍልቶ እና አቀዝቅዞ መጠቀም እንዲችል ህብረተሰቡን ማስተማር ይኖርብናል ብለዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በበኩሉ በዚህ አመት ብቻ 15ሺ ሰዎች በውሃ ወለድ በሽታ ተጎጂ ሆነዋል፡፡

ምንጭ፡-አናዶሉ የዜና ወኪል

 

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3527384
  • Unique Visitors: 199330
  • Published Nodes: 2627
  • Since: 03/23/2016 - 08:03