በክልል ደረጃ የሚወጡት ህጎች፣ ደንብና አዋጆች ከህገመንግስቱ ጋር እንዳይለያዩ የክልሉ ህገመንግስት ተርጓሚ ኮሚሽን ትልቅ ሃላፊነት እንዳለበት የኢፌዲሪ የፌደሬሽን ምክር ቤት ባለሙያዎች ተናገሩ፤ ለክልሉ ህገመንግስት ተርጓሚ ኮሚሽን የአቅም ግንባታ ስልጠናም ተሰጥቷል፡፡

ባህር ዳር፡ ግንቦት 22 /2009 ዓ/ም(አብመድ)ሃገሪቱ የምትከተለው ፌዴራላዊ ስርዓት ማንኛውም ህግ ፣ደንብና አዋጅ በክልል እና በፌደራል ደረጃ ሊወጡ እንደሚችሉ ህገመንግስቱ ይደነግጋል ፡፡ 
የሚወጡ ህጎች ጨምሮ የሰባዊ መብት እና የመንግስት የስልጣን አሰጣጥ ሂደት ላይ የሚወሰኑ ውሳኔወች ከህገመንግስቱ ጋር እንዳይጣረሱ መጠንቀቅ እንደሚያስፈልግ ባለሙያዎቹ ይገልጻሉ ፡፡
የክልሉ ህገመንግስት ተርጓሚ ኮሚሽን የአቅም ግንባታ ስልጠና ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ይርሳው ታምሬ እንዳሉት‹‹ የህጎች ሁሉ የበላይ የሆነውን ህገመንግስት የመተርጎም ሃላፊነት የተሰጣችሁ አካላት ናችሁ፡፡ እናንተ የምትወስኑት በክልሉ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል፡፡ ትክክለኛ ትርጉም በሰጣችሁ ቁጥር በክልሉ የህገመንግስቱ መጠበቅ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ›› ብለዋል ፡፡
የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ የህግ አማካሪ አቶ ወልዱ መርኔ እንደሚሉት በአንቀጽ 50 ንሁስ አንቀጽ 7 ላይ ክልሎች የዳኝነት ስልጣን እንዳላቸው ይደነግጋል ስለዚህ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክልላዊ ጉዳዮች በሆኑ ክርክሮች ላይ ስልጣን አለው፡፡ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድቤት በስልጣኑ ስር በሚሆኑ ጉዳዮች የሚሰጠው ውሳኔ ህገመንግስቱን የሚቃረን ከሆነ ለትርጉም ይቀርባል ብለዋል፡፡
የፌደሬሽን ምክር ቤት የህገመንግስት ትርጉም እና የማንነት ጉዳይ ዳይሬክተር አቶ ሙሉየ ወለላው በበኩላቸው እንዳሉት የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የህገመንግስት ጉዳይ አጣሪ ጉባኤ ለማቋቋም እና የአሰራር ስርአቱን ለመወሰን የሚረዳ አዋጅ መውጣቱ ክልሉ የራሱን መብት ተጠቅሞ ህግ ይተረጉማል፤ ህግ ለመተርጎም እገዛ ያደርጋል፤ የዜጎች መብትም እንዳይጣስ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
በስልጠናው ላይ የተሳተፉ ህግ ተርጓሚዎች በበኩላቸው ስልጠናው ህግ ለመተርጎም የሚያስችል አቅም እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 2827046
  • Unique Visitors: 178997
  • Published Nodes: 2512
  • Since: 03/23/2016 - 08:03