በክልሉ ከ366 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተና ይቀመጣሉ፡-የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ

ባህር ዳር፡ ግንቦት 19/2009 ዓ/ም(አብመድ)በአማራ ክልል ከ366 ሺህ በላይ ተማሪዎች ክልላዊና ብሄራዊ ፈተና እንደሚወስዱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል
፡፡
የቢሮው ሀላፊ አቶ ይልቃል ከፋለ እንደገለፁት ተማሪዎች ዓመቱን ሙሉ ሲማሩ የከረሙትን በክፍል፣ በክልላዊ ፈተናና በብሔራዊ ፈተና ግንቦትና ሰኔ ወር ትምህርታቸውን ያጠናቅቃሉ፡፡ 
8ኛ ክፍል ከ311 ሺህ በላይ የሚሆኑ ፣10ኛ ክፍል 284 ሺህ 203፣ 12ኛ ከፍል 71 ሺህ 304 በአጠቃላይ ከ366 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ያስፈትናል፡፡

እንደ አቶ ይልቃል ገለፃ ፈተናውን በተረጋጋና ሠላማዊ በሆነ መንገድ ለመስጠት ተገቢ የሆኑ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች የተከናወኑ ሲሆን በተለይ ብሔራዊ ፈተናዎች በጥንቃቄና ደህንነታቸው በተረጋገጠ መንገድ ተዘጋጅተው ታትመው አሁን በመሠራጨት ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ፈተናውን ለማስተዳደር የሚያስፈልጉ የክላስተር አስተባባሪዎች የጣቢያ ኃላፊዎች ሱፐር ቫይዘሮችና ፈታኞች በአግባቡና በጥንቃቄ ተመልምለውና ተለይተው ስለፈተናው አሰጣጥ እና አሠራር ኦረንቴሽን በመውሰድ ላይ ይገኛሉ፡፡


ፈተናው ሠላማዊና የተረጋጋ ሆኖ እንዲከናወን ተገቢው ቅድመ ዝግጅት በትምህርተ ቤት ደረጃም በፀጥታ ክፍሉም እየተካሄደ ይገኛል፡፡ እስካሁን ድረስም ያሉት አፈፃፀሞች ፈተናው በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት እንዲሰጥ ተገቢው ቅድመ ዝግጅቶች በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ ብለዋል አቶ ይልቃል ፡፡

 

ተማሪዎች ክልላዊም ይሁን ብሔራዊ ፈተና ከሌሎች የክፍል ፈተናዎች የተለየ አለመሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡ ስለዚህ የሚያስጨንቃቸው የሚረብሻቸው አንዳችም ምክንያት የለም፡፡ ይህን በደንብ መረዳት አለባቸው፡፡ ስለዚህ ያጠኑትን ጥናት ተረጋጋተው በንፁህ ህሊናቸውና በራሳቸው ብቻ ፈተናቸውን መፈተን አለባቸው፡፡

 

ወላጆች፣ መምህራንና የትምህርት ቤቱ አመራርም ተማሪዎች ሳይረበሹ ፈተናቸውን በአግባቡ እንዲወስዱ አስፈላጊው ቅድመ ዝግድት የተደረገ መሆኑን ለተማሪዎች መግለፅና ማስረዳት እንደሚጠበቅባቸው ቢሮ ሃላፊው ተናግረዋል፡፡

 

ተማሪዎች ዓመቱን ሙሉ ሲያጠኑና ሲዘጋጁ ቆይተዋል፡፡ መምህራንም ተማሪዎችን ለማዘጋጀተ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ ስለዚሀ በትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ ሙሉ በሙሉ ተዘጋጅተዋል፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3537585
  • Unique Visitors: 199679
  • Published Nodes: 2652
  • Since: 03/23/2016 - 08:03