በክልሉ ከ1ሺህ በላይ አመራሮች ላይ እርምጃ ተወስዷል-አቶ ንጉሱ ጥላሁን

በክልሉ ከ1ሺህ በላይ አመራሮች ላይ እርምጃ ተወስዷል-አቶ ንጉሱ ጥላሁን

ባሕር ዳር፡የካቲት 21/2008 ዓ/ም (አብመድ)በአማራ ክልል በመልካም አስተዳደር ላይ ችግር በፈጠሩ ከ1 ሺህ 300 በላይ አመራሮችና ባለሙያዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮሚኒዩኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በሰጡት ወቅታዊ መግለጫ ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት አስታውቀዋል፡፡

702 አመራሮች በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃ ላይ የሚገኙ666ቱ ደግሞ ባለሙያዎች መሆናቸውን ገልዋጸል፡፡ ከላይ የተጠቀሱት አመራሮችና ባለሙያዎች ከሀላፊነታቸው የተነሱ ሲሆን በ47 ላይ ደግሞ በድሲፕሊን ተጠያቂዎች ሆነዋል፡፡16 አመራሮች ደግሞ ብህግ ተጠያቂ ሆነዋል ብለዋል አቶ ንጉሱ ጥላሁን፡፡
እርምጃ ከተወሰደባቸው ውስጥ 245 ፖሊሶች ፣89 ዳኞች ፣19 አቃብያነ ህግ ናቸው፡፡ከሃላፊነታቸውም ተነስተዋል፡፡

በአጠቃላይም በክልሉ በተደረገው የመልካም አስተዳደር ንቅናቄ ከ1ሺህ 300 በላይ አመራሮችና ባለሙያዎች ከሀላፊነታቸው ተነስተው ተጠያቂ ሆነዋል ተብሏል፡፡

ከሥራ ማገድ፣ ከደረጃ ዝቅ ማድረግ፣ ወደ ሌላ ቦታ ማዛወር፣ በህግና በዲስፕሊን እንዲጠየቁ ማድረግ ደግሞ ከተወሰዱት እርምጃዎች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

አቶ ንጉሱ እንዳሉትም በስፋት የነልካም አስተዳደር ችግር የታየባቸው ተቋማትም፡1ኛ/የፍትህ ስርዓት አስፈጻሚ ተቋማት፡-አቃቢ ህጎች .ፖሊስ፣ፍርድቤት፣2ኛ/መሬት አስተዳደር 3ኛ/የንግድ ስርዓቱ እና የገቢ ስርዓት ተቋማት አብዛኛውን ድርሻ ይይዛሉም ተብሏል፡፡

እርምጃው መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ህብረተሰቡን በማሳተፍ በተፈጠረው የንቅናቄ መድረክን ተከትሎ የተወሰደ ነው፡፡

 

 

 

 

Amhara Mass Media Agency's photo.

በመድረኩ ህብረተሰቡግር ያለባቸውን አካላት በመጠቆምና መረጃ በማቀበል ከፍተኛ ተሳትፎ ማድረጉም ተመልክቷል፡፡

በንቅናቄ መድረኮቹም ከ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ህዝብ መሳተፉን አስታውሰዋል፡፡ 
እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልጧል፡፡

መላኩ ሙሉጌታ

በአማራ ቴሌቪዥን ፣በአማራ ራዲዮ እና በኤፍኤም ባህር ዳር 96.9 ዜናዎች እና ዝግጅቶች ዙሪያ ለሚኖርዎት ጥቆማና አስተያየት ለአማራ ቴሌቪዥን(ATVን)፣ ለአማራ ራዲዮ(ARን) እና ለኤፍኤም ባህር ዳር 96.9 (FMን) በማስቀደም በ8200 ማድረስ ይችላሉ፡፡

 

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3872471
  • Unique Visitors: 214892
  • Published Nodes: 2859
  • Since: 03/23/2016 - 08:03