በእስራኤልና ፍልስጤም መካከል ሰላም እንዲሰፍን አሜሪካ የተቻላትን ታደርጋለች፡-ፕሬዝዳንት ትራምፕ

ባህር ዳር፡ ግንቦት 15/2009 ዓ/ም(አብመድ)የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሳኡዲ አረቢያ ጉብኝታቸው በኋላ በቀጥታ ወደ እስራኤል- ቴልአቪቭ በማቅናት ከእስራኤልና ፍልስጤም መሪዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል ፡፡


ፕሬዝዳንቱ በቴልአቪቭ ከሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር ተገናኝተው ከተወያዩ በኋላ በቀጣይ የፍልስጤም አስተዳደር መሪ የሆኑት ሙሃሙድ አባስን አነጋግረዋል ፡፡ 
እስራኤልና ፍልስጤም ላለፉት ሶስት ዓመታት የሰላም ውይይት ሣያደርጉ መቆየታቸው በአካባቢው ውጥረት ተባብሶ እንዲቀጥል ቢያደርግም ያሁኑ ጉብኝታቸው ሁኔታውን ሊቀይር እንደሚችል ትራምፕ ተናግረዋል ፡፡
ከእስራኤልና ፍልስጤም መሪዎች ጋር ባነሷቸው ክልላዊ ጉዳዮች አዎንታዊ ምላሽ ያገኙት ፕሬዝዳንት ትራምፕ በአካባቢው ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ሃገራቸው አሜሪካ የተቻላትን ሁሉ ታደርጋለች ብለዋል ፡፡
የፍልስጤሙ አባስ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የተቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ቃል ሲገቡ ቤንያሚን ኔታንያሁም በሰላም ማስፈን ዙሪያ ተመሳሳይ ርዕይ እንደሚኖራቸው ገልጸዋል ፡፡ የትራምፕ ወደአካባቢው መምጣትም ለሰላም ሂደቱ ጥሩ አጋጣሚ ሊፈጥር እንደሚችል ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል ፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3537630
  • Unique Visitors: 199679
  • Published Nodes: 2652
  • Since: 03/23/2016 - 08:03