በቻግኒ ከተማ የመሰረተ ልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥሉ-ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን

ባህር ዳር፡ ግንቦት 16/2009 ዓ/ም(አብመድ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቻግኒ ከተማ የተሰሩ የመሰረተ ልማትና ኢንዱስትሪዎችን ሲመርቁ እንዳሉት ከተማዋ በትክከለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች፤በለውጥ ጎዳና ውስጥ ገብታለች፡፡ፋና ወጊስራዎች ተጀምረዋል፡፡ድህነትንና ኋላ ቀርነትን ለማሽነፍ ሁሉም በየአካባቢው ያለውን እየወረወረ ለተሻለ ብልጽግና እየተጋ ይገኛል፡፡ለብልጽግና ከተጠቀምንበት አመቺ ግዜ ነውም ብለዋል፡፡ብልሆች ያላቸውን እያስተባበሩ የሚጎላቸውን ለመሙላት ክንዳቸውን አስተባብረው እየተንቀሳቀሱ እጅግ አመርቂ በሆነ ጉዞ ውስጥ ገብተዋል፡፡ከእነዚህ ውስጥ አንዷ የቻግኒ ከተማ ስለሆነች እጅግ በጣም የሚያበረታታ የብልሆችን መንገድ ተሳፍራለች፡፡

ወጣቱን የስራ ባለቤት የሚያደርጉና የአካባቢውን ጸጋዎች የሚጠቀሙ የጥጥ ማዳመጫና የዱቄት ፋብሪካ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተመርቀዋል፡፡

እየተከናወኑ ያሉ የመሰረተ ልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮነን አሳስበዋል፡፡

የጥጥ ማዳመጫ ፋብሪካው ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ሰኢድ ስሩር ማዳመጫ መከፈቱ ጥጥ ከቤንሻንጉልና ከፓዊ ስለሆነ የምናመጣው የአካባቢውንም አርሶ አደሮች ይጠቅማል በርካታ ወጣቶችንም የስራ ተጠቃሚ ያደርጋል ፡፡ነገር ግን የመብራት መቆራረጥ በስራችን ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እየፈጠረ ነው ብለዋል፡፡

ነዋሪዎች በበኩላቸው የጠየቅነው የመሰረተ ልማት ጥያቄ ምልሽ በማግኘቱ ተደስተናል ፡፡በአጭር ጊዜም ለውጥ መጥቷል ብለዋል፡፡

 

 

ወንድአጥር መኮንን

ተጻፈመሰረት አስማረ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3158954
  • Unique Visitors: 186665
  • Published Nodes: 2579
  • Since: 03/23/2016 - 08:03