በሴራ ሊዮን የደረሰውን የጎርፍ አደጋ ተከትሎ የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ እርዳታ ጠየቁ፡፡

ባህር ዳር፡ ነሀሴ 13/2009 ዓ/ም (አብመድ)በሴራ ሊዮን የደረሰው የጎርፍ አደጋ ቀናት ቢያስቆጥርም አለማቀፉ ማህበረሰብ እያደረገ ያለው እርዳታ አነስተኛ እና ቀርፋፋ ሚባል ነው የሚሉት ፕሬዝዳንት ኤርነስት ባ ኮሮማ ሴራሊዮን ከምንጊዜውም በላይ አሁን የአለማቀፉን ማህበረሰብ እርዳታ ትፈልጋለች ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ እርዳታ ለማግኘት አስፈላጊውን ጥሪ ለአለማቀፉ ማህበረሰብ ባስተላልፍም እስካሁን እዚህ ግባ የሚባል እገዛ እያገኘን አይደለም ሲሉ ያላቸውን ቅሬታ ይፋ አድርገዋል፡፡

ጋና "ወደ ሴራ ሊዮን እርዳታ የላከች  ቀዳሚ ሀገር ስትሆን የጋና ፕሬዝዳንት ናኖ አኮፋዶ ወደ 400 ገደማ የሚሆኑ ህዝቦችን የገደለ እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከቤት ንብረታቸው ያፈናቀለውን የጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት ተከትሎ ሀዘኑ የሁሉም አፍሪካውያን ነው ካሉ በኋላ በቻልነው መጠን ተጎጅዎችን ለመርዳት እንረባረባለን ብለዋል ፡፡በአደጋው የሟቾች ቁጥር እየጨመረ እንደመጣ እና አሁንም መሬት ውስጥ ተዳፍነው የሞቱ የሴራሊዮን ዜጎች ሊኖሩ እንደሚችሉ የተገመተ ሲሆን ፍለጋው ግን አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ እና አልጀዚራ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3527316
  • Unique Visitors: 199328
  • Published Nodes: 2627
  • Since: 03/23/2016 - 08:03