በማንቸስተር እንግሊዝ በደረሰ የአጥፍቶ መጥፋት አደጋ የ22 ሰዎች ህይወት አለፈ

ባህር ዳር፡ ግንቦት 15/2009 ዓ/ም(አብመድ)በጥቃቱ ከ50 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል፡፡ በማንቸስተር አሬና ላይ በሽብርተኞች አቀናባሪነት እንደተከናወነ በሚጠረጠረው የሽብር ጥቃት 22 ሰዎች ተገድለዋል፡፡ ከ 50 በላይ ደግሞ ቆስለዋል፡፡ ጥቃቱ ሰኞ ምሽ ላይ የተፈጸመ ሲሆን ለአሜሪካዊቷ የፖፕ አቀንቃይኝ አሪያና ግራንዴ በተዘጋጀ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ጥቃቱ የተፈጸመው፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አምበር ሩድ አረመኒያዊ ድርጊት ነው ሲሉ ጥቃቱን ኮንነዋል፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው ጥቃቱ በተደጋጋሚ የሚፈጸመው ለአደጋ ተጋላጭ በሆኑ የህብረተሰብ ክፍላችን ውስጥ ነው ፡፡ ጥቃቱ በአንድ ግለሰብ አማካኝነት ይፈጸም እንጅ ከሽብርተኝነት ጋር ያለውን ግንኙነት እያጣራን ነው ብለዋል፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3161831
  • Unique Visitors: 186711
  • Published Nodes: 2579
  • Since: 03/23/2016 - 08:03