በሊቢያ በኩል አድርገው ሲጓዙ የነበሩ 900 ስደተኞች የመስጠም አደጋ አጋጠማቸው

ባህር ዳር፡ ሰኔ 12 /2009 ዓ/ም (አብመድ)

በሊቢያ አቋርጠው አውሮፓ ለመድረስ በመሞከር ላይ የነበሩት 900 የአፍሪካ እና የእስያ ስደተኞች ካሰቡት ሳይደርሱ የመስመጥ አደጋ አጋጥሟቸዋል የባሕር ኃይል ቃል አቀባዩ እንደገለፁት፡፡

የባሕር ኃይል ቃል አቀባዩ ጄነራል እዮብ ቃሲም እንዳሉት ከእንጨት በተሰራ ጀልባ በመሆን ባሩን ለማቋረጥ የሞከሩት ህገወጥ ስደተኞች አዘዋዋሪዎች ጀልበዋ ከአቅሟ በላይ 906 ስደተኞችን እንድትይዝ በማድረግ ለመንቀሳቀስ በመሞከራቸው ነው የመስመጥ አደጋ የገጠማቸው፡፡

እንደ ጀኔራል ቃሲም ገለጻ ከሆነ ከስደተኞቹ መካከል ሰባት ነፍሰ ጡር እናቶችን ጨምሮ 25 ልጆች እና 98 ሴቶች ይገኙበታል፡፡

አካባቢው ከ2011 የሙሃመድ ጋዳፊ መንግስት ውድቀት በኋላ ለህገወጥ አዘዋዋሪወች ምቹ ስፍራ እየሆነ መምጣቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

የመስመጥ አደጋ ቢያጋጥማቸውም የህገወጥ ስደተኞቹ ህይወት ሳያልፍ የነፍስ አድን ስራው መጠናቀቁን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡-ሮይተርስ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 1440466
  • Unique Visitors: 92861
  • Published Nodes: 1596
  • Since: 03/23/2016 - 08:03